የሲቪል ሰርቪሱን አቅም ከመገንባት አኳያ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 9/2017 ዓ.ም፡- የሲቪል ሰርቪሱን አቅም ከመገንባት አኳያ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጋር በጋራ እንደሚሰራ ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ገለጹ፡፡ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ እና ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አልማዝ መሰለ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝተዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ለኮሚሽነሩ እና ምክትል ኮሚሽነሯ የአስተዳደሩን ምርትና አገልግሎቶች አስጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱም አስተዳደሩ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎች የሚያኮሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡

ኢመደአ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ከማድረግና ደህንነቱን ከማስጠበቅ አኳያ በርካታ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርቶችን ማበልጸጉን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ለሁሉም የመንግስት ተቋማት ተደራሽ መሆን እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

ከጉብኝቱ ቀጥሎም የኢመደአን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻ የተደረ ሲሆን በዉይይቱ ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ አብረው ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸወን ጉዳዩች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የሲቪል ሰርቪሱን አቅም በቴክኖሎጂ ከመገንባት አንፃር በተለይም የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እና ደህንነቱን ከማረጋገጥ አንጻር አስተዳደሩ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በበኩላቸው አስተዳደሩ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ የሚያስደስት እና የሚያኮራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ይህንን አፈፃፀም በላቀ ደረጃ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ክቡር ኮሚሽነሩ አያይዘው እንደገለጹት ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከማሳደግና ባሕል ከመገንባት አኳያ የሲቪል ሰርቪስ አመራሮች እና ሰራተኞች በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚሰለጥኑበት መድረክ በቀጣይነት ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በሌላም በኩል የአስተዳደሩ የቴክኖሎጂ ምርቶች ተገቢው ዋጋ ወጥቶላቸው ለሁሉም ሀገራዊ የመንግስት ተቋማት ተደራሽ መደረግ እንደሚገባቸውና ለዚህም ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም በኢመደአ የተገነባው የሕዝብ ቁልፍ መሰረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI) በመንግስት ተቋማት ላይ ተግባራዊ መደረግ እንደሚኖርበት፤ በተለይም መሶብ ላይ የገቡ ተቋማት ሁሉም በአስገዳጅ እንዲተገብሩት ከሲቪል ሰርቪስ በኩል አቅጣጫ መሰጠቱን ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት አስተዳደር ፖሊሲ የሪፎርም የትግበራ ምዕራፍ ላይ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በዚህ ረገድ ቀጣይ የሚሰሩ ሥራዎች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ እና ደህንነቱ እንዲረጋገጥ በማስቻል ረገድ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በበርካታ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡