የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን (ኢመደአ) ጎበኙ::

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለልዑካን ቡድናቸው አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፤ አስተዳደሩ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን አስጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ ቀጥሎም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በሳይበር ደህንነት መስክ ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ሆርጌ ሉዊስ በኢመደአ ያደረጉት ጉብኝት እንዳስደነቃቸው ገልጸው በተለይም አስተዳደሩ በታዳጊዎች ላይ እየሰራ የሚገኘው የታለንት ልማት ሥራ ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን መስክ ያስቀመጠችው ራዕይ ዕውን እንደሚሆን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ኩባ ለረዥም ዓመታት የዘለቀና በደም የተሳሰረ ጠንካራ ዲፕሎማሲ ግንኙነትና ወዳጅነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ በቀጣይም በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋራ በጋራና በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት በሳይበር ደህነት ዘርፍ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በሳይበር ደህንነትና ዲጂታላይዜሽን መስክ በሁለቱ ሀገራት ያለውን አቅም ልምድ ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት፤ በተለይም ደግሞ በቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት፣ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል በቀጣይነት በጋራ ማልማት በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ውጤታማ የሆነ ውይትት ማድረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ በኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን፤ ከዚሁ ጎን ለጎን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች