ራዕይ እና ተልዕኮ
Vision and mission
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ)
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የሀገራችንን የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማቶች ከጥቃት በመከላከል ብሔራዊ ጥቅሞችን እንዲያስጠብቅ በሚል ዓላማ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 130/1999 መሰረት ተቋቋመ፡፡
ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ የመጣውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከል እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የኤጀንሲውን ተግባርና ኃላፊነት እንደገና ማሻሻል በማስፈለጉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 250/ 2003 እንዲሁም በቅርቡ በአዋጅ ቁጥር 808/2006 እንደገና ተቋቁሟል፡፡
ተልዕኮ (Mission)
የአገሪቱን ኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ - ልማት ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሄራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ
ራዕይ (Vision)
የኢንፎርሜሽን የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችል ብሔራዊ አቅም እውን ሆኖ ማየት
እሴቶች (Values)
- አይበገሬነት / Resilience
- ልዩነት መፍጠር / Making Difference
- ተዓማኒነት / Integrity
- ክብር መስጠት / Respect for the people
- የህግ ተገዥነት /Respect for the law