ሳይበር ትንኮሳ

ሳይበር ትንኮሳ (Cyber Bulling)

የሳይበር ምህዳሩ ይዞልን ከመጣው መልካም  አጋጣሚ  በተጨማሪ  አሉታዊ  ጎኑም ሌላኛው  ገጽታው ነው፡፡                                                     

ልንጠቅሳቸው ከምንችላቸው  አሉታዊ ጉኖች መካካል በተጠቃሚዎች ላይ  የሚደርሱትን  ትንኮሳዎች ማንሳት እንችላለን፡፡

 የሳይበር ትንኮሳ  ማለት ቴክኖሎጂን  በመጠቀም  ሆን ብሎ የሰዎችን  ስሜት የሚረብሽ ወይም  ስነ-ልቦና  የሚጎዱ መልዕክቶችን፤ መረጃዎችን  ወይም ፎቶዎችን   ማስተላለፍ እና  መለጠፍን የሚያጠቃልል ተግባር ነው ፡፡  ይህ ተግባር በብዛት  በስሜትም ሆነ በአስተሳሰብ  ባልበሰሉ ታዳጊዎች  ወጣቶች እንዲሁም አዋቂዎችላይ የሚከሰት ከመሆኑ የተነሳ   የሚያደርሰው   ጉዳት ከፍ ያለ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ  የሳይበር  ምህዳሩ ማንነታቸውን አንዲደብቁ ከማስቻሉ  የተነሳ ሰዎች  በቀላሉ  ሌላውን ሰው አንዲተነኩሱ እድል ይፈጥራል፡፡ እንደነዚህ አይነት  ስሜት የመረበሽ ወይም የማስፈራራት  ባህሪይ ያላቸው መልዕክቶች  ሰዎች ላይ በተለይም በታዳጊ ወጣቶች  ላይ ከፍተኛ  የስነ-ልቦና ቀውስ ያስከትላሉ፡፡

በዋናነት ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ እንዲሆንና በራስ መተማመናቸው እንዲቀንስ ያደርጋል፤ በቀጣይ ከሰዎች ጋር በሚኖራቸው ማህበራዊ ግንኙነት ላይ መፍራት ወይም ተነሳሽነት ማጣት፤ በሳይበሩ  አለም የሚደርሰው ማስፈራራት በገሃዱ አለም እንደሚደርስባቸው በማሰብ መፍራት እና መረበሽ፤ ተቀባይነት አንዳጡ መሰማት  እና እራሳቸውን ማግለል፤ ድብርት   ..  የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ከዚህ አይነት ጥቃት ራስን ለመጠበቅ ከሚረዱን ዘዴዎች ውስጥ ከማናቃቸው ሰዎች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት መወሰን፤ የግል መረጃንም ሆነ ሚስጢርን በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ አለማስፈር፤ ወላጆች የልጆቻቸውን  ኢንተርኔት አጠቃቀም እና የሚያሳዩትን  የባህሪ ለውጦች መከታተል፤ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች  ሪፖርት እንድናደርግ የሚያስችሉንን ቅንብሮች መጠቀም፤አዋቂዎችን”  ለተሻለ እርዳታ ማማከር ይጠቀሳሉ፡፡  

Asset Publisher