የናይጀሪያ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን በኢመደአ ትምሕርታዊ ጉብኝት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የናይጀሪያ ሎጂስቲክስና ማኔጅመንት ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን (ኢመደአ) ጎበኙ፡፡

የልዑኩ መሪ ኮሎኔል አዲቦዬ ከጉብኝቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ለማጠናከር ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎች፤ በተለይም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎችና በተጨባጭ የተመዘገቡ ስኬቶች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ናይጀሪያ ጠንካራና መልካም የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው እንደሆነ የገለጹት ኮሎኔል አዲቦዬ፤ በቀጣይም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የየሀገራቱንም ሆነ የአፍሪካን የሳይበር ደህንነት ሁለንተናዊ አቅም ማጠናከር እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የናይጀሪያ ሎጂስቲክስና ማኔጅመንት ኮሌጅ ከፍተኛ መኮንኖች ልዑካን ቡድን በየዓመቱ የሚያደርጉትን ዓለማቀፋዊ እና ወታደራዊ ጉብኝት በኢትዮጵያን እያካሄዱ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች