የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች የኢመደኤን የለውጥ ሥራዎች ጎበኙ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ በመገኘት በተቋሙ የተሠሩ የለውጥ ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛው ኢመደኤ በሪፎርም የሰራቸውን ሥራዎች ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮች ገለጻ አድርገዋል፡፡በገለጻቸው ስለተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ ቁልፍ የሥራ መስኮች፣ በሪፎርም የተሰሩ ሥራዎች እንዲሁም የኤጀንሲውን ዋና ዋና የትኩረት መስኮች አብራርተዋል፡፡

ኢመደኤን በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም ለማድረግ በሰው ኃይል፣ በአሠራር ሥርዓት እና በቴክኖሎጂ ላይ ልዩ ትኩረት በመሥጠት እየተሰራ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በበኩላቸው በኢመደኤ የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውንና አጠቃላይ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ራዕይ የሚያሳኩ ሥራዎችን ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በለውጥ ሥራ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህን የለውጥ ሥራ እውን በማድረግ በኩል ከኢመደኤ በርካታ ተሞክሮዎችን እንዳገኙ እና በቀጣይም በጋራ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ / ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን የለውጥ ሥራ በማገዝ ረገድ ኮርፖሬሽኑ ከኢመደኤ የሚጠብቃቸውን ማናቸውንም ድጋፎች በቀጣይነት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢመደኤ የተሰጠው ሀገራዊ ኃላፊነት ትልቅ እንደሆነና ይህንን ኃላፊነትም በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ በተግባር ማየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በጉብኝታቸው የኢመደኤን ኢትዮ-ሳይበር የተሰጥኦ፣ የምርትና አገልግሎት ማሳያ ኤግዚብሽን ማዕከል እንዲሁም ምቹ የሥራ አከባቢ በመፍጠር በኩል እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን በሥራ ክፍሎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ በአጠቃላይም በነበራቸው ጉብኝት መደሰታቸውን እና ለተቋማቸው ግብዓት የሚሆኑ በርካታ ተሞክሮዎችን እንደወሰዱ ገልጸዋል፡፡

Most Viewed Assets