የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ!!

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን #GreatEthiopianHomeComing ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሀገር ቤት የመጣችሁና በመምጣት ላይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ!!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /INSA እንኳን በደህና መጣችሁ እያለ ዲያስፖራው ወደ እናት ሀገሩ ሲመጣ በተለያዩ አግባቦች እናት ሀገሩን ለማገዝና የበኩሉን አሻራ ለማሳረፍ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ሀገራችሁን አቅማችሁ በፈቀደ መጠን በተለያየ መስክ ለማገዝ በመምጣታችሁ ኤጀንሲው የተሰማውን አድናቆት እየገለፀ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲም በኢንፎርሜሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የሚሠራ ተቋም እንደመሆኑ መጠን በዘርፉ በእውቀታችሁ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች ቴክኒካል ጉዳዮች ለማገዝ እና የራሳችሁን አበርክቶ ማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ ተቋማችን በደስታ የሚቀበል እና የሚያስተናግዳችሁ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

በዚህ ጉዳይ ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመሥራት የምትፈልጉ የዲያስፖራ አባላት በ "አዲስ ዲያስፖራ ማዕከል" በኩል ወይም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /INSA/ በቀጥታ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች /+251910012912 ወይም +251904049633 / ማናገር የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ!

የሳይበር ደህንነት የጋራ ኃላፊነት ነው!!