ህወሐት ለአንበጣ መንጋ መከላከል ሥራ በሚል ወደ ትግራይ ክልል ድሮን አስገብቶ ለእኩይ ተግባር ሊያውል እንደነበረ ኤጀንሲዉ ገለፀ

የህወሐት አጥፊ ቡድን ለአንበጣ መንጋ መከላከል ሥራ በሚል ሰው አልባ በራሪ ቁስ /ድሮን/ ወደ ክልሉ አስገብቶ ለእኩይ ተግባር ሊያውል አቅዶ እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገለፁ፡፡

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል በሚል ድሮን ለማስገባት ተሞክሮ እንደነበር ዶ/ር ሹመቴ አውስተዋል፡፡

ቆይቶ በተደረገ ምርመራ ድሮኑ ለእኩይ ተግባር ሊውል እንደነበር የሚያሳዩ አመላካች መረጃዎች በመገኘታቸው ፈቃዱ መታገዱን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው ኤጀንሲው ይህን በማድረጉ ሊከሰት ይችል የነበረን ጉዳት ማስቀረት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው በተሰጠው ሀገራዊ ተልዕኮ ሳምንቱን ሙሉ ለሀያ-አራት ሰዓት እና ለሰባት ቀናት በመስራትና የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ በጥፋት ቡድኑ ሊቃጡ ይችሉ የነበሩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል እንደቻለም ዶ/ር ሹመቴ ገልጸዋል፡፡

ከጥቃቶቹ መካከልም ሀገርን ለማተራመስ የሚያስችሉ የሀሰት መረጃዎች ከማሰራጨት ባለፈ ጨምሮ የደህንነት ሽፋን በሌላቸው ድረ-ገጾችን ላይ የተሞከሩ ጥቃቶች እንደሚገኙበትም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ኪዚህ በሻገር የጥፋት ቡድኑ በመንግስት የሚዲያ ተቋማት መሠረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ምንም ዓይነት የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ሥራ እንዳይሮር ጥረት ሲያደርግ እንደነበረ የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡

Most Viewed Assets