ኢመደአ በሀገሪቱ ካሉ 317 የህጻናት ማቆያ ማዕከሎች መካከል ሞዴል ማዕከል በመባል እውቅና ተሰጠዉ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የህጻናት ማቆያ ማዕከል በሀገሪቱ ካሉ 317 የህጻናት ማቆያ ማዕከላት መካከል ሞዴል የህጻናት ማቆያዎች ካሏቸዉ ተቋማት አንዱ በመሆን በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እውቅና ተሰጠዉ።

በዚህም የኢመደአ የህጻናት ማቆያ ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ከሆኑ ማዕከላት መካከል የ2ኛ ደረጃን አግኝቷል።

ይህን እዉቅና የተሰጠዉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ማቆያና መንከባከቢያ ማዕከላት ማቋቋሚያ መስፈርት እና አሰራር ለመወሰን የወጣ መመሪያ 1084/2017 ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመምከር በተዘጋጀ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ።

በመድረኩም ለኢመደአና ሌሎች ሞዴል ለሆኑ የህጻናት ማቆያ ማዕከላት የእዉቅና ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን፤ ኢመደአ የሁለተኛ ደረጃን በመያዝ እዉቅና የተሰጠዉ በተለይ ስታንዳርዱን የጠበቀ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት በመስጠት፣ ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ ለማካፈል በሩን ክፍት በማድረግ፣ በሀገራችን ለተቋቋሙ በርካታ የህጻናት ማቆያ ማዕከላት መቋቋም አበርክቶ በማድረግ ነው፡፡

የአንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተቋማዊ ምቹ ከባቢን ከመገንባት አኳያ በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎችን የሚሰራ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ለአስተዳደሩ አመራርና አባላት ስታንዳርዱን የጠበቀ የሕጻናት ማቆያ ማዕከል በመገንባት ሥራ ላይ አውሏል፡፡ ማዕከሉ ከአስተዳደሩ በተጨማሪ በአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት ለሚገኙ ሌሎች ሦስት ተቋማት አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች