ፌስቡክ ገጽ ላይ የሐሰት መረጃ ወይም ከማህበረሰቡ እሴቶች ጋር የማይሄዱ ይዘቶችን ሪፖርት ለማድረግ ልንከተለው የሚገባ ቅደም ተከተል ምንድነው?

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

ከማህበረሰቡ ባህል እና አብሮ የመኖር እሴቶች ጋር አብረው የማይሄዱ ነገሮች ሲያጋጥሙን ለፌስቡክ ካምፓኒ ሪፖርት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ፌስቡክ ካምፓኒም ከተጠቃሚዎቹ የሚቀርቡለትን ሪፖርቶች መሠረት በማድረግ ገጾቹን እንዲዘጉ ወይም የተለጠፉ ይዘቶች እንዳይታዩ ያደርጋል፡፡

በፌስቡክ ሪፖርት የሚደረግባቸው እና የማህበራዊ ትስስር ገጹን የአጠቃቀም ፖሊሲ የሚጥሱ ጉዳዮች የሚታወቁ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ለአብነት የጥላቻ ንግግሮች፣ ብጥብጥና ሁከት የሚያስነሱ ይዘቶች፣ እርቃን ገላን የሚያሳዩ ምስሎች ወይም ሌሎች መሰል ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ፌስቡክ ላይ ግብረ-ገብነት የጎደላቸዉ እና እኩይ የሆኑ ይዘቶችን ሪፖርት ማድረግ የጥላቻ ንግግሮች እንዳይስፋፉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡

በመሆኑም እነዚህን ከማህበረሰቡ እሴት እና ከስነ-ምግባር ያፈነገጡ ይዘቶች ሪፖርት ለማድርግ ቀጥሎ በቅደም ተከተል የተቀመጡ ተግባራትን ማከናወን ያስፈልጋል።

ሪፖርት ለማድረግ፡-

1. ሪፖርት ማድረግ የምንፈልገው ገጽ ወይም ይዘት ላይ መሆን ወይም ይዘቱን መክፈት፤
2. ከዚያም "Find Support or Report Post/Link" የሚለውን ትዕዛዝ መጫን፤
3. በመቀጠል "Report" በሚል አርዕስት ስር ከዚህ በታች ከተገለጹት ውስጥ የትኛውን አፈንጋጭ ይዘት ልናመለክት እንደፈለግን እንድንመርጥ "Please select a problem" የሚል ትዕዛዝ ይቀርብልናል፡፡ ሪፖርት የሚደረግባቸው የችግር አይነቶችም በዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበው እናገኛለን፡-

• እርቃን ገላን የሚያሳዩ ምስሎች /Nudity/፣

• ብጥብጥ የሚያስነሱ ይዘቶች /Violence/፣

• ትንኮሳ /Harassement/፣

• እራስን ማጥፋት ወይም በራስ ላይ ጉዳት ማድረስ /Suicide or self-

Injury/፣

• ሐሰተኛ መረጃ /False Information/፣

• አስፈላጊ ያልሆነ መልዕክት /Spam/፣

• ህገወጥ ሽያጭ /Unauthorized Sales/፣

• የጥላቻ ንግግር /Hate Speech/፣

• ሽብርተኛነት /Terrorism/

4. ከላይ ከቀረቡልን ችግሮች ውስጥ ሪፖርት ማድረግ የምንፈልገውን

ትዕዛዝ ስንጫን የችግሩን ዓይነት በዝርዝር የሚጠይቅ/ የሚያቀርብ

ሌላ መዘርዝር ይመጣልናል፤

5. ለምሣሌ "ብጥብጥ የሚያስነሱ ይዘቶችን /Violence/" መርጠን

ብንጫን ምን አይነት ብጥብጥ /What kind of Violence?/ የሚል

ጥያቄ የሚቀርብልን ሲሆን በማስከትል፡-

 • በምስል የተደገፈ ብጥብጥ /Graphic Violence/፣
 • ሞት ወይም ከባድ ጉዳት /Death or severe injury/፣
 • ሁከት አነሳሽ /Violent threat/፣
 • እንስሳትን ማጥቃት /Animal abuse/፣
 • ሌላ ጉዳይ /Something else/ የሚሉ ምርጫዎች ያመጣሉ፡፡
6. ከላይ ከቀረቡት አንዱን ስንጫን ወይም ሪፖርት ስናደረግ ሪፖርት የምናደርግበትን ጉዳይ ምንነት እና ካምፓኒው ሪፖርት ያደረግነው

ርዕሰ-ጉዳይ ምን ሀሳቦችን የያዘ ሲሆን እርምጃዎችን እንደሚወስድ የሚገልጽ ጽሑፍ የሚያስነብበን ሲሆን አንብበን እንደጨረስን ማረጋገጫ መልዕክት እንዲደርሰን የሚያግዝ "Submit" የሚል ትዕዛዝ እንድንጫን ይጠይቀናል፤

7. ትዕዛዙን እደተጫንን ሪፖርት እያደረግንበት ስላለነው ገጽ ወይም ግለሰብ "Thank you, we’ve received your report" የሚል ይመጣልናል፤
8. እዚሁ መልዕክት ላይ "Next" የሚል ትዕዛዝ ስንጫን ተጨማሪ አማራጮች "More Option" ያቀርብልናል፤
9. በቀረበልን አማራጭ መሠረት ሪፖርት እያደረግንበት ያለውን ገጽ ወይም ግለሰብ "Block" ማድረግ፣ አለመከተል "Unfollow"፣ አለመውደድ "Unlike" ወይም ፌስቡክ ጉዳዩን እንዲመለከተው ብቻ

"Submitted to Facebook for Review" የሚሉ አማራጮች ውስጥ አንዱን በመጫን ጨርሰን እንወጣለን፡፡

በአጠቃላይ የፌስቡክ ገጽ ላይ የሀገር አንድነት እና ሉኣላዊነትን ለመሸርሽር ሆነ ተብለው የተከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ የትስሰር ገጾች እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ሪፓርት በማድረግ፣ ባላማጋራት እና ሌሎች ጋር እንዳይደርሱ በማድረግ ሁሉም ራሱንም ሆነ ማህበረሰቡን እንዲጠብቅ ኤጀንሲው ለማስገንዘብ ይወዳል፡፡