ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ  ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢመደኤ) “ከሳይበር እስከ ግንባር” በሚለዉ መርሃ ግብሩ በወሎ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ።

በግንባር በመገኘት ለሰራዊቱ ድጋፉን ያስረከቡት የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ኢመደኤ እና መከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ስራዎችን እንደሚሰሩ አዉስተዉ ከህልዉና ዘመቻዉ ጋር ተያይዞ የኢትዮጳያን አንድነት ለማጽናት አጥንቱን እየከሰከሰ፣ ስጋዉ እየበጣጠሰ፣ደሙን እያፈሰሰ ለሚገኝዉ ሰራዊታችን ደ ደጀንነታችን እና ወገንተኛንታችንን ለማሳየት ይህን ድጋፍ ይዘን እዚህ ተገኝተናል ብለዋል።

ኢመደኤ በሚታዩም በማይታዩ ጉዳዮች ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ዶ/ር ሹመቴ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቅማችሁ የቻላችሁ ሁሉ ተከተሉኝ ባሉት መሰረት እኛም በህልዉና ዘመቻዉ የምንሳተፍባቸዉ በርካታ ጉዳዮች መኖሩን በመረዳት “ከሳይበር እስከ ግንባር” የሚል መርሃ ግብር በመቅረጽ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል።

ኤጀንሲዉ የኢትዮጵያን ዲጂታል ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ስራዎች እየሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከዚህ ጎን ለጎን በማህበራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ መሆኑ ጠቁመዉ በማሳያነትም ከፍተኛ አመራሩ እና አባላቱ በየ3 ወሩ ሳያቋርጡ ለመከላከያ ሰራዊታችን የደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በዚህ መርሃ ግብር በደብረ-ብርሃንና አዲስ አበባ ለሚገኙ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የሰራዊታቸን አባላት የምሳ ግብዣ ፣ በደብረ-ብርሃን ለሚገኙ ከቀያቸዉ ለተፈናቀሉ ሴቶች፣ ህጻናት እና አቅመ ደካሞች የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ደግሞ በግንባር በመገኘት ጀግናዉን የመከላከያ ስራዊታችንን ለማበረታታት ድጋፍን በአካል ይዘን መተናል ብለዋል።

ሰራዊቱ ሰሞኑን አለምንን ያስደመመ ድል ማድረጋቸዉን የገለጹት ዶ/ር ሹመቴ ሁልጊዜም ቢሆን “ከእናንተ ጋር መሆን ከብር ነዉ እናንተም የሃገር ክብር ናችሁ” ብለዋል።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰባተኛ እዝ የቀለብ እና ንብረት ክፍል ሃላፊዉ ኮሎኔል ሙስጠፋ የሱፍ በበኩላቸዉ ኢመደኤ የመከላከያ አንድ አካል አድርገን ነዉ ምንወስደዉ ያሉ ሲሆን በሳይበሩ አለም የሃገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከሚያደርገዉ ጦርነት፣ለመከላከያ ከሚያስታጥቀዉ የቴክኖሎጂ ምርቶች ባሻገር ለመከላከያ ሰራዊቱ ወገንተኝነቱን ለማሳየት ግንባር ድረስ ድጋፍ ይዞ በመመጣቱ በእዙ ስም አመሰገናለሁ ብለዋል።

ከድጋፍ መርሃ ግብሩ ጎን ለጎን የኤጀንሲዉ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በግንባር በመግኘት በመረጃ ጦርነቱ ላይ እየተሳተፉ ያሉት አባላቱን የጎበኘ ሲሆን በወራሪዉ ጁንታ ላይ እየተወሰደ ባለዉ የመደምሰስ እና የማጥራት ስራ የናንተ ድርሻ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በማዉሳት የስራ ባልደረቦቻቸዉን አበረታተዋል።

ኢመደኤ በመጀመሪያ ዙር “ከሳይበር እስከ ግንባር” በሚለዉ መርሃ ግብሩ ከ3.2 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸዉ ድጋፎችን ከአዲስ አበባ እስከ ግንባር ላሉ ወግኖቻችን ድጋፍ አድርጓል።