የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሃገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርቶችን በቀዳሚነት ሊጠቀም ይገባል - የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ፡ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሃገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርቶችን በቀዳሚነት በመጠቀም ሃገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድን በማሳካት በኩል የራሳቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ተናገሩ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በኢመደአ የበለጸገውን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሞባይል መተግበሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ አያይዘው እንደገለጹት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትን ደህንነቱ በተጠበቀ ሃገር በቀል ቴክኖሎጂ በማስታጠቅ የም/ቤቱን አሰራሮች ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ረገድ ኢመደአ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡ የም/ቤቱ አባላትም የታጠቋቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከየትኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት በመጠበቅ ረገድ አስፈላጊውን የደህንነት መፍትሄ በመተግበር የራሳቸውንም የሆነ የሃገርን የሳይበር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ከረዩ ባናታ በኢመደአ የበለጸገው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሞባይል መተግበሪያ ላይ ለም/ቤቱ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡ በዚህም የሞባይል መተግበሪያው የም/ቤቱን ዋና ዋና ሥራዎች ማለትም ሕግ የማውጣት ሥራ፣ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ፣ የዜጎችን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ የማድረግና ምላሽ የማሰጠት ሥራ እንዲሁም ሌሎች ሥራዎችን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የጊዜ፣ የወጪ እና የጉልበት ብክነትን የሚያስቀር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የም/ቤት አባላቱ ይህንን መተግበሪያ በመጠቀም የም/ቤቱን አጠቃላይ መረጃዎች በቀላሉና ተደራሽ በሆነ መልኩ የሚያገኙ ሲሆን ከዚህም ባለፈ ከም/ቤቱ ጽ/ቤት የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶችም በተመሳሳይ በቀላሉና በተቀላጠፈ መንገድ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ሲሉም አቶ ከረዩ ባናታ ተናግረዋል፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን በተመለከተ በቀረበው ገለጻ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የም/ቤቱ አባላት እንዳሉት ኢመደአ የሃገርን ተጨባጭ ችግር የሚፈቱ በርካታ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን የሚያበለጽግ ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ይህ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሞባይል መተግበሪያም የም/ቤቱን አሰራሮች ዘመናዊና ቀልጣፋ ከማድረጉም በላይ በደህንነቱ በኩልም የውጭ ሃገር የቴክኖሎጂ ምርቶችን ከመጠቀም ይልቅ ሃገር በቀል በሆነ ተቋም የተሰራ በመሆኑ አስተማማኝ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሃገር በቀል የቴክኖሎጂ ምርቶችን በቀዳሚነት በመጠቀም ሌሎች ተቋማትም እንዲጠቀሙ አርአያ ሊሆን እንደሚገባም የም/ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር በቀላሉ የሚገናኙበት፣ የወከላቸውን ሕብረተሰብ ጥያቄዎች የሚሰበስቡበትና ምላሽ የሚያሰጡበት እንዲሁም ዜጎች የመረጧቸው ተወካዮቻቸው ጋር በቀላሉና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የሚገናኙበት የሞባይል መተግበሪያም በቀጣይ እንደሚለማና አገልግሎት ላይ እንደሚውል በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች