ሀገራት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ጥሪ አቀረቡ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ "የመንግስታት፣ የሲቪል ማህበራት እና የንግድ ማህበረሰቦች ትብብር ዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነትን ለማረጋገጥ" በሚል ርእስ ከመስከረም 7-9 /2016 ዓ.ም በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት መንግስታት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው በተለይም የሳይበር ቴክኖሎጂው በየጊዜው መራቀቅ የሰውን የአኗኗር ዘይቤ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አስተሳሰቦችን ጭምር እየቀየራቸው እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ የቴክኖሎጂው እያደገ መምጣት ለኢኮኖሚው፣ ለፖለቲካው፣ ለባህሉና ለማህበራዊ መስተጋብሩ አወንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ሁሉ አሉታዊ ጎንም እንደሚኖረው አቶ ሰለሞን ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ሰለሞን አያይዘውም አሁን ላይ ሁሉም ሐገራት ተግባራቸውን ለማከናወንና ከሌላው ዓለም ለመገናኘት የዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ግድ እያላቸው ከመምጣቱም በላይ አንድ ሐገር ደሴት ሆኖ ተገልሎ መኖር እንደማይችል ሁሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂው ያመጣቸውን መልካም አጋጣሚዎች እና የሚያስከትለውን የደህንነት ስጋት በጋራ መምከር አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

ድንበር የለሽ እና ወስብስብ ተፈጥሮ ያለውን የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ሐገራት በተናጠል በሚያደርጉት ጥረት ማረጋገጥ እንደማይችሉና ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ቀጠናዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ይኸውም ትብብራችን፤ እውቀታችንን፣ ልምዳችንን እና ሪሶርሳችንን በማስተባበር ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር ዓለምን መፍጠር ያስችላል ሲሉ አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡

አቶ ሰሎሞን ሶካ በመልዕክታቸው መጨረሻ እንደገለጹት፤ ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረችው፣ ከአፍሪካ ሁለተኛውን ግዝፉን የሕዝብ ቁጥር ይዛ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች የምትገኘው ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት አጀንዳን ፈጽሞ ቸል እንደማትል ተናግረው፤ ለዚህም በዋናነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከማቋቋም አንስቶ፣ ፖሊሲዎችን መቅረጽ፣ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ መደንገግን እንዲሁም የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ይሁንና የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች ለመፍታት በተናጠል ከምናደርገው ጥረት ይልቅ ከተለያዩ ሐገራት ጋር በትብብር የምንፈጥረው አቅም የተሸለ በመሆኑ መንግስታት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher