የጀርመኑ የፌደራል የሳይበር ደህንነት እና የሳይበር ዲፕሎማሲ ቢሮ ከኢመደአ ጋር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የጀርመን የሳይበር ደህንነት እና የሳይበር ዲፕሎማሲ ቢሮ ሃላፊ ጆን ሬልስ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ጋር በዘርፉ በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም በሳይበር ደህንነት እና በሳይበር ዲፕሎማሲ ከአፍሪካ ሀገራት በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር በመረጃ ልውውጥ፣ በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር እንዲሁም በሳይበር ደህንነት እና ሳይበር ዲፕሎማሲ አቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ሀገራቸው ያላትን ፍላጎት ሚስተር ጆን ሬልስ ገልጸዋል፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በሳይበር ምህዳር ላይ አለም አቀፍ የህግ ጥሰቶች እየተፈፀሙ መምጣታቸውን ተከትሎ ይህን ችግር ለመቅረፍ በሀገራት መካከል የትምምን መፍጠሪያ እርምጃዎች (confidence building measures) ዙሪያ ለመስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው የሳይበር ደህንነትን ከማረጋገጥ አንጻር ኢትዮጵያ ያላትን አሁናዊ ቁመና ያብራሩ ሲሆን በተለይም የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ እስትራቴጂ እና እስታንዳርድ በማዘጋጀት እና ተግባራዊ በማድረግ የሄደችበትን ርቀት አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷን ለማረጋገጥ መከላከልን መሰረት ያደረገ እስትራቴጂ እንደምትከተል ያመላከቱት አቶ ሰለሞን ሶካ ይህንን ለማስፈፀም ተተኪ የሳይበር ኃይል ከመገንባት አንፃር በሳይበር ታለንት ማእከል በተከታታይ ዓመታት የተሰሩ ፍሬያማ ስራዎችን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በሳይበር ዲፕሎማሲ መስክ በሀገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የሳይበር ዲፕሎማሲ ምክክሮች (IGAD ,UN ,African Union (Malabo Convention) ላይ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ እያደረገች ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

አቶ ሰለሞን ሶካ እና የጀርመን የሳይበር ደህንነት እና ሳይበር ዲፕሎማሲ ቢሮ ኃላፊ ጆን ሬልስ ካደረጉት ውይይት ባሻገር ኢመደአ ሀገራዊ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፣ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን ጐብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኀላ ሚስተር ጆን ሬልስ በስጡት አስተያየት ተቋሙ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራቸው ባሉ ስራዎች ላይ መደስታቸውን ገልፀው፤ በተለይም በሳይበር ታለንት ማእከል በታዳጊዎች ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎች ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት በተምሳሌትነት የሚገለጽ ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ስንዝረዋል፡

Asset Publisher