Blog Details

blog

Electronic Signature Regulation Approved by the Council of Ministers

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ደንብን አጸደቀ።
የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010ን ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ ስርዓቶችን በአዋጁ እና በተሻሻለው የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1358/2017 መሰረት ግልፅ እና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ለመተግበር እንዲያስችል ሆኖ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

በሌላም በኩል የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ የተወያየ ሲሆን፤ ስትራቴጂው ለዜጎች አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግና መሰረተ ልማቶቹን ለማስፋፋት፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በተሻለ መንገድ ማሳካትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

Social Share :