የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ተቀባይነት በማግኘት እውቅና ተሰጠው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ፓሰፖርትን ደህንነት ለማስጠበቅ አገልግሎት ላይ የዋለው የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን (Country Signing Certificate Authority - CSCA) ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን በማግኘት እና ICAO በሚያስተዳድረው ማዕከላዊ የሰርተፊኬት ቋት (Public Key Directory (PKD)) ውስጥ በማካተት በመላው አለም ጥቅም ላይ እንዲውል እውቅና ተሰጠው።

በካናዳ ሞንትሪያል በተከናወነዉ የእዉቅና ስነስርዓቱ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድን ጨምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሃላፊዎች በተገኙበት አስፈላጊውን መስፈርቶች በማሟላት አለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም እንዲዉል እውቅና ተሰጥቶታል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን የዲጂታል ደህንነት በማጠናከር ረገድ ትልቅ እርምጃ የወሰደውን በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI) ዳታ ማዕከል ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በመገኘት መመረቃቸዉ የሚታወስ ነው።

ይህንን የቁልፍ መሰረተ ልማት ዳታ ማዕከል በይፋ መመረቁን ተከትሎ ኢመደአ አገልግሎት መስጠት ለመጀመር የሚያስችለውን ተግባራት በማከናወን የካቲት 11/2017 ዓ.ም ለኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት እና ለዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት የሚውል “የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን (Country Signing Certificate Authority - CSCA) አገልግሎትን በይፋ ማስጀመሩ ይታወቃል።

በዚህም አገልግሎት ለኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ህትመት የደህንነት ማረጋገጫ የሚሆን ዲጂታል ሰርተፊኬት በማዘጋጀት እና ለኢፌዲሪ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በመስጠት የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትን ደህንነት የማረጋገጥ ተግባሩን እውን አድርጓል።

ይህንን አገልግሎት መጀመር ተከትሎ ከደህንነት በተጨማሪ አገልግሎቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና ተአማኒነት እንዲኖረው የሚያስችለዉን እዉቅና የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከሚያስተዳድረዉ ማዕከላዊ ሰርተፍኬት ቋት ዉስጥ እንዲካተት በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲዉል እዉቅና አግኝቷል።

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች