በህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች የስልክና ኮምፒውተር አጠቃቀማችን በምን መልኩ ሊሆን ይገባል?
በህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች የስልክና ኮምፒውተር አጠቃቀማችን በምን መልኩ ሊሆን ይገባል?
ስማርት ስልኮችን፣ ኮምፒውተሮችን ወይም ታብሌቶችን ህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች ላይ መጠቀም በመኖሪያ ቤት ወይም በቢሮ ውስጥ እንደመጠቀም ሊታይ አይገባም፡፡
የራስዎን መሣሪያዎች /devices/ ይሁን በኢንተርኔት ካፌ ወይም በቤተ-መፅሐፍት ውስጥ በሚያገኟቸውን መሣሪያዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ የሚጠቀሙ ከሆነ በርካታ የደህንነት ስጋቶች ሊያጋጥምዎ ይችላል፡፡
ስለዚህ በህዝብ የጋራ መጠቀሚያ በሆኑ መሣሪያዎች /devices/ ስንጠቀም፡-
• እንደ ክሬዲት ካርድ ቁጥሮች ያሉ ጠቃሚ የይለፍ-ቃሎችን ወይም የግል መረጃዎችን ሊያሳዩ የሚችሉ የገንዘብ ግብይቶችን ያስወግዱ፤
• በተቻለ አቅም እምነት የማይጣልባቸው የህዝብ ኮምፒውተሮችን ከመጠቀም በፊት ሰላይ አጥፊ ሶፍትዌሮችን /Spyware/ ለመፈተሽ ወይም ለመቃኘት ታማኝ የድር አጥፊ ሶፍትዌሮች ማጽጃ ፕሮግራሞችን ይጠቀሙ፤
• በይነ-መረብ እየተጠቀሙ ከነበረ ፋይሎችን እና ኩኪዎችን /Cookies/ የሚሰርዝ ማፈላለጊያ መጠቀምዎን እና ቅኝት ያደረጉበትን ማፈላለጊያ ታሪክ ማጽዳቶን ያረጋግጡ፤
• የኢንተርኔት አማራጭ የሚያፈላልጉባቸውን እና የሚጠቀሙባቸውን ማናቸውም የይለፍ -ቃላት ደህንነት ይጠብቁ፤ ጥርጣሬ ካለዎት የማፈላለጊያውን እገዛ አማራጭ ይጠቀሙ፤
• ወደ ቤትዎ ከተመለሱ በኋላ በህዝብ ኮምፒውተር ላይ የተጠቀሙባቸውን ማናቸውም ዓይነት የይለፍ-ቃላት መቀየር እንዳለብዎት አይዘንጉ፡፡
• እንደ Gmail፣ Hotmail ወይም Yahoo ያሉ የድር መልዕክት መለዋወጫ አካውንት የሚጠቀሙ ከሆነ እና የተላከልዎን መልእክት (ኢ-ሜይልዎን) ለማየት ከፈለጉ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የድር አገናኝ /web link/ መጠቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ፤
• ከበስተጀርባዎ ቆመው የሚጠቀሙትን መረጃ የሚመለከቱ ሰዎች አለመኖራቸውን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡