የምክር ቤቱ ሥራዎች በቴክኖሎጂ ሊደገፉ ይገባል - የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ፤ የምክር ቤቱን ሥራዎች በቴክኖሎጂ መደገፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

አፈ-ጉባዔው ይህንን የተናገሩት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና የአይሲቲ ባለሙያዎች ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከፍተኛ አመራሮች ጋር አዲስ በለሙ የሞባይል መተግበሪያዎች ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

የምክር ቤቱ ስራዎች ወረቀት አልባ እንዲሆኑ እና የተቋሙ ቁልፍ መረጃዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ተይዘው እንዲጠበቁ ታስቦ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) አማካኝነት የለማው የሞባይል መተግበሪያ ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን የተከበሩ አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት እርስ በእርሳቸው የሚገናኙባቸው እና የሕዝብ ውክልና ስራዎችን በማቀላጠፍ ውጤቱን በቀላሉ ማየት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በ2015 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ሲሆን ቅድሚያ ለምክር ቤት አባላት እና ለዘርፉ ባለሙያዎች አስፈላጊው ስልጠና እንደሚሠጥ ነው አፈ-ጉባዔው ያስገነዘቡት፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው፤ ኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከለውጡ ማግስት የራሱን ሪፎርም በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ የሀገሪቱ ደህንነት በአስተማመኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ በትጋት እየሰራ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይም በሚያከናውናቸው ተግባራት ለሌሎች ሀገሮች ተምሳሌት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ምክትል አፈ-ጉባዔዋ አክለውም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጠቀምባቸው የለሙ ቴክኖሎጂዎች ምን ያህል ሚስጥራዊና ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው የሚለው በትኩረት ሊፈተሽ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትልልቅ ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚወስን ተቋም በመሆኑ INSA የምክር ቤቱ ስራዎች እንዲሻሻሉ እና መረጃዎቹ በሚስጥር እንዲያዙ አስቦ ያለማቸው ቴክኖሎጂዎች ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በአንጻሩ እነዚህ የለሙ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ የሚጭበረበሩ እና ሚስጥራዊ ተጋላጭነት እንዳያስከትሉ በትኩረት ሊታዩ እንደሚገባ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል፡፡

ለምክር ቤቱ የለሙ ቴክኖሎጂዎች ለአጠቃቀም ግልጽ መሆን እንዳለባቸው እና ተቋማዊ ሊሆኑ እንደሚገባ የጠቆሙት ደግሞ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ናቸው፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገሪቱ ትልቁ ተቋም በመሆኑ የሚያከናውናቸው ተግባራት እንዲዘምኑ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የበኩሉን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከውጭ ሀገራት በግዥ መልክ ከሚያስገባቸው ሲስተሞች በስተቀር በተቋሙ የሚለሙ ቴክኖሎጂዎችን ምክር ቤቱ እንዲጠቀም ያለምንም ክፍያ ፈቅደናል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችም የሳይበር እና መሰል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ቅድሚያ ከተከበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልምድ እንዲቀስሙ እንፈልጋለን ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ አክለዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች