የፀደይ ባንክ የመረጃ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የፀደይ ባንክ የመረጃ ማዕከል (Data Center) ግንባታ ተጠናቆ ሥራ ጀምሯል፡፡ በባንኩ የመረጃ ማዕከል ምረቃ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (/) ባስተላለፉት መልዕክት ፀደይ ባንክ ዓላማውን ለማሳካት የግብርናውን ዘርፍ መደገፍ እና ልማትን ማፋጠን ቀዳሚ ድርሻው መኾን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ተደራሽ እንዲኾን መረጃ ትልቅ ሀብት በመኾኑ ፀደይ ባንክ መረጃ የሚሰበሰብበትን፣ የሚከማችበትን፣ የሚሰራጭበትን እና በጥንቃቄ የሚያዝበትን ማዕከል ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ መሥራቱ የተለየ እና ተመራጭ ያደርገዋል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

በባንኩ የዳታ ማዕከል ምረቃ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) /ዋና ዳይሬክተር / ትግስት ሀሚድ እንዳሉት የፋይናንስ ተቋማት ከዲዛይን ጀምሮ የሳይበር ደህንነት ስራን ማቀናጀትና ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ኢመደአ የባንኩን የመረጃ ማዕከል በሚገነባበት ወቅት ሙሉ የማማከር ስራን ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት /ዋና ዳይሬክተሯ የቴክኒክ ቡድንም ተቋቁሞ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የዲዛይን፣ የፋይናንስ እና የቴክኒክ ስራውንም በሀላፊነት መስራቱን / ትግስት ሀሚድ ገልፀዋል።

የሳይበር ላይ መረጃ መንታፊዎች በተለይም የፋይናንስ ተቋማትን ዒላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ከዚህ አኳያ ተቋማቱ የሳይበር ደህንነታቸውን ከዲዛይን ጀምሮ ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል ሲሉ /ዋና ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡

/ ትግስት ሀሚድ አያይዘው እንደተናገሩት የፀደይ ባንክ የመረጃ ማዕከል ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም የተገነባ መኾኑን ጠቁመው ባንኩ ያስገነባው የመረጃ ማዕከል ከሌሎች ባንኮች ጋር ተወዳዳሪ እንደሚያደርገውም ነው የገለጹት፡፡

ኢመደአ የፀደይ ባንክ የመረጃ ማዕከሉን ዴሊቨሪ አይሲቲ ቴሌኮም መሠረተልማት ያከናወነ ሲኾን አይቪኮም ቴክኖሎጂ ደግሞ የዳታ ማዕከሉን እና የማገገሚያ ማዕከሉን መገንባቱን ተገልጿል፡፡

የፀደይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መኮንን የለውምወሰን በባንኩ የመረጃ ማዕከል ምርቃት ላይ እንደተናገሩት ጸደይ ባንክ 270 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል ገንብቶ ማጠናቀቁን ተናግረዋል። "የመረጃ ቁልፍ ሀብት ቢኾንም በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋለ ግን ጥቅም የለውም" ያሉት አቶ መኮንን የተገነባውን የመረጃ ማዕከል በአግባቡ እና ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለመጠቀም የባንኩ በርካታ ባለሙያዎች በቂ ስልጠናዎችን ወስደዋል ብለዋል።

የተገነባው የመረጃ ማዕከልም አቅሙ ከፍ ያለ እና ለረጅም ጊዜ በአግባቡ የሚያገለግል እንደኾነ ጠቁመዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች