የኤጀንሲዉ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ በዛሬዉ ዕለት ተመረቀ

 

 

የኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር / አብይ አህመድ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በምርቃ ስነ-ሥርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋምን የመፍጠር ጅማሮ ዛሬ በኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ህንጻ በመመረቅ መጀመራቸዉን እና ኢንሳም በአፍሪካ ዉስጥ ካሉ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከሚሰሩ ተቋማት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ መሰረተ ልማቶች እንዲኖረው ተደርጎ መገንባቱን ገልጸዋል፡፡

 

"ኢንሳ ዉስጥ የማየዉ ኢትዮጵያን ነዉ" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ተቋሙ ሲመሰረት ትዉልድን መሻገር እንዲችል 26 ብሄር ብሄረሰቦች የተዉጣጡ አባላትን በማቀፍ እንዲመሰረት መደረጉንም አዉስተዋል፡፡

ኢመደኤ ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ በነበረዉ የህንጻ ኪራይ እስከ አሁን አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ የኪራይ ወጪ ማዉጣቱን እና ይህም ከአጠቃላይ ለህንጻዉ ግንባታ ፕሮጀክት ከወጣዉ 50 በመቶ ገደማ ሊሸፍን ይችል እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር / ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸዉ "ግንባታዉ ህንጻ ብቻ ሳይሆን ህልም የተፈታበት ህንጻ ከመሆኑም ባሻገር የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲሁም የጥልቅ እሳቤ ባለቤትነት የተገለጹበት ነዉ" ብለዋል

 

የኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛዉ በበኩላቸዉ የህንጻዉ ተገንብቶ መጠናቀቅ ከኢመደኤ በተጨማሪ ሰላም ሚኒስቴር፣ አርተፍሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል፣ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በአጠቃላይ መንግስት ለእነዚህ ተቋማት ለህንጻ ኪራይ የሚያደርገዉን ወጪ በማስቀረት ለሌሎች የመንግስት ስራዎች እንዲዉል ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነዉ ብለዋል፡፡