የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ የሳይበር ደህንነት ወር በስኬት መጠናቀቅን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጡ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 

ሁለተኛዉን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የጋራ ሃላፊነት ለሳይበር ደህንነት እንወቅ እንጠንቀቅ”። ባለፉት 30 ቀናት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አዘጋጅነት ሲከበሩ ቆይተዋል።

የሳይበር ደህንነት ወሩ መጠናቀቁን ተከትሎ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ  ለጋዜጠኖች መግለጫ ሰጥተዋል።  በዚህም ባለፈዉ አንድ ወር ዉስጥ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሳይበር ደህንነት ወር ሲከብር መቆይቱን የጠቆሙት የኤጀንሲዉ  ዋና ዳይሬክተር በተቀመጠዉ እቅድ መሰረት ስራዎች መሰራታቸዉን እና ተቁሙ ያስቀመጣቸዉን ግብ መምታቱን ገልጸዋል።

የሳይበር ደህንነት ወር በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ መከበሩን ያውሱተ ዋና ዳይሬክተሩ  በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 18 ጊዜ መከበሩን ገልጸዋል።  2ኛዉ የሳይበር ደህንነት ወር ከመጀመሪያዉ የሳይበር ደህንነት ወር አከባበር አንጻር እጅግ ብዙ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ እና የሚፈለገዉን ግብ ማሳካተ ያስቻለ ስራ መሰራት መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በሁለተኛዉ የሳይበር ደህንነት ወር ሲከብር ሶስት ዋና ዋና አላማዎችን ይዞ መነሳቱን ያውሱት ሃላፊዉ ከእነዚህ መካከልም፥

 1. የመጀመሪያዉ ተቋማት እና በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ከመቸዉም ጊዜ በተሻለ መልኩ ንቃተ ህሊናቸዉን እንዲያሳደጉ ፣ እንዲያዉቁ እና እንዲያሳዉቁ የማድረግ የተሰሩ በርካታ ስራዎች መስራት መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ደረጃም በሁለተኛዉ የሳይበር ደህንነት ወር በሚገባ ማሳካት መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሹመቴ ጠቁሟል። የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ  ከሰዉ ይጀምራል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከሰዉ ተነሰቶ ወደ ቡደን ተቋም እና ወደ ሃገር ያድጋል ብለዋል።
 2. ሁለተኛዉ “ተቋማት” ናቸዉ ያሉት ሃላፊዉ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሏቸዉ እንዲሁም የአሰራር ስርአትን የሚከተሉ የተቋማቱ ጉዳት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ በተለየ ሁኔታ ውሳኝ ብለን የለየናቸዉ  ናቸዉ። ኤጀንሲዉ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም እንኳ ተከታታይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች መስራት ቢቻልም በዚህኛዉ የሳይበር ግንዛቤ ወር በጣም በርካታ የሆኑ መንግስታዊ ተቋማትን ተደራሽ ከማድርግ አንጻር ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። በዚህም የተቋማቱን አመራሮች በማግኘት ስለጉዳዩ አሳሳቢነት የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ከመስራት እና አብረን ልንሰራባቸዉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ መግባባት ተችሏል ተብሏል።
 3. ሶስተኛዉ የሳይበር ደህንነት ጉዳይ የሁሉም ሃላፊነት ነዉ የሚለዉን በሁሉም ዜጋ ማስረጽ መሆኑን ያወሱተ ዶ/ር ሹመቴ። በዚህ የሳይበር ደህንነት ወርም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሳይበር ደህነንት ላይ ከሚሰሩ አካላት ጋር በጋራ ሊሰሩ ይገባል በሚል ሰፊ ስራዎች መሰራታቸዉን ገልጸዋል። የሳይበር ምህዳሩ በበሃሪዉ አንዱ የሚገባዉን ሰረቶ አንዱ ጋር ስህተት ቢፈጠር ሌላዉን ለጥቃት ሊያጋልጠዉ ስለሚችል የሁሉንም ጠንቃቄ እና ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም መጠንቅ ፣ መተባበር እና ቅንጅታዊ አሰራር ያስፈልገናል። ከዚህ ባለፈ መናበብ ፣ መረዳዳት እና መደጋገፍ ያስፈልገናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ። በዚህ እሳቤ አማካኝነትም መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በትብብር እና በቅንጅት ስራዎች እንድንሰራ ለማደርግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሉ ዶ/ር ሹመት ገልጸዋል። በሳይበር ወሩም ቅንጅታዊ ስራዎችን ከማጠናከር አንጻር ያሉ አቅሞችን በመለየት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ተብሏል።

 

እንደ አጠቃላይ በሳይበር ወሩ የተለያዩ ፕረዘንቴሽኖች የቀረቡ ሲሆን ከፕረዘንቴሽኑ በኋላም ኤግዚቢሽን እንደነበር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ኤግዚቢሽን የተለያዩ አጋር አካላት ኤጀንሲዉ እየሰራዉ ስላለዉ ስራዎች መመልከት መቻላቸዉን ጠቁመዋል።

ኤጀንሲዉ ደህንነታቸዉ የተጠበቁ የሳይበር ደህንነት ምርቶችን በማልማት ለሚመለከተዉ አካል ማድረስ እና በጋራ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ይህም ተቁሙ ብቻዉን የሚሰራዉ ስራ አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል። በዘርፉ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን እያሳተፍን ጠቃሚ የሆኑ የቴክኖሎጂ መርቶችን እያመረትን የሃገሪቱን የሳይበር ምህዳር ደህንነት ማስጥበቅ እንድትችል ሁላችንም በርብርብ እንሰራለን ሲሉ ሃላፊዉ ጠቁመዋል።

በሁለተኛዉ የሳይበር ደህንነት ወርም በርካታ ግብአቶች መገኘታቸዉ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከኤጀንሲዉ ጋር በተያያዘ ብዥታ የነበራቸዉ ሁሉ በዚህ በግንዛቤ ማስጨበጫ ወሩ ስለ ኤጀንሲዉ በደንብ ተገንዝበዉ ገብረ-መልስ የሰጡ እንዳሉም በመግለጫዉ ተነስቷል።

በአሁኑ ሰአት የዲጂታል ሉአላዊነት ትልቅ የአለማችን ጉዳይ መሆኑን ያወሱት ዶ/ር ሹመቴ በተለይም ደግሞ ሌት ከመር አድቫንቴጅ ተጠቅምን ወደ ዘርፉ እየገባን ያለን ሃገሮች በጣም በጥንቃቄ ልንገባበት እና ልንከዉነዉ ይገባል ብለዋል። የዲጂታል ሉአላዊነት የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ እየሆነ መምጣቱን ያወሱት ሃላፊዉ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ደግሞ በምንም አይነት መልኩ ለድርድር ሚቀርብ አይደለም ብለዋል።

 

በሳይበር ምህዳሩ ዉስጥ ያለዉን አወንታዊ ሚና በግለሰብ ደረጃ በአግባቡ መወጣት ስንችል እንዲሁም የተቋማታችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ ከቻልን የሃገራችንን ደህንነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ ችለናል ማለት ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ሃገራችንን ከሳይበር ደህንነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ ተችሏል ይህም በሌላ መልኩ የሃገሪቱን ዲጂታል ሉአላዊነት ማስጠበቅ ተችሏል ማለት ነዉ።

በሁለተኛዉ የሳይብር ደህንነት ወር የታዩትን መልካም እድሎች ቀምረን ለሶስተኛዉ የሳይበር ደህንነት ወር ስናከብር ባልፉት ዝግጅቶች ተምረን እንዲሁም ከሌሎች ሃገሮች ተሞከሮ ወስደን በሃገር አቀፍ፣ በቀጥናዊ እና አለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሶስተኛዉን የሳይበር  ደህንነት ወርን በከፍተኛ ልህቀት ይከበራል ብለዋል።  ቀጣዩን የሳይበር ደህንነት ወር የላቀ እንዲሆን የሚያደረግዉ በዘርፉ ያሉ ተዋንያኖች የግንዛቤ እና ምህዳሩን የመጠቀም ፍላጎት ከፍ ማለቱን ተከተሎ ነዉ ብለዋል።

“የጋራ ሃላፊነት ለሳይበር ደህንነት እንወቅ እንጠንቀቅ”።