"በዊንዶዉስ" ላይ የደህንነት ክፍተት መከሰቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ዝመና እንዲያደርጉ ማይክሮሶፍት አሳሰበ

አዲስ አበባ መስከረም 14/2013፡ በዊንዶዉስ ላይ ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጥ ክፍተት የተከሰተ ሲሆን የዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ የደህንነት ዝመና/updates/ እንዲያደርጉ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡
የዊንዶዉስ ሰርቨር ላይ የዜሮሎጎን /Zerologon/ ተጋላጭነት መከሰቱንም ማይክሮሶፍት ገልጿል፡፡
ዜሮሎጎን የተባለዉ የደህንነት ክፍተት የመረጃ መንታፊዎች የተጠቃሚዎችን ዶሜን /domain/ በርቀት ሆነዉ ለመቆጣጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንዲመነትፉ የሚረዳ ተጋላጭነት ነዉ፡፡
በመሆኑም የዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች ሊደርስ የሚችለዉን የመረጃ ጥቃት በመረዳት በአስቸኳይ የደህንነት ዝመናዎችን እንዲተገብሩ ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡

Most Viewed Assets