ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን የኤጀንሲው አመራሮች እና አባላት በዛሬው ዕለት አከበሩ

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን የኤጀንሲው አመራሮች እና አባላት በዛሬው ዕለት አከበሩ

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 7/2013- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ አመራሮችና አባላት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በዛሬው ዕለት በኤጀንሲው ቅጥር ግቢ አክብረዋል፡፡

ዕለቱን የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛዉን ጨምሮ የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ተከቧራል፡፡

/ ሹመቴ በስነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የሴቶች መብት ማከበር ያለበት ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቀን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሴቶችን እና መብታቸዉን ተገድን ሳይሆን ማክበር ያለብን አውቀንና ክብር እንደሚገባቸው አምነን ሊሆን ይገባል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሴቶችን መብት የሚያከበር ማህበረሰብ ለመፍጠር ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋማት ያሉ ሁሉም አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢመደኤ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር / ፅጌሬዳ ወርቁ በበኩላቸው ባስተላፉት መልዕክት ተቋሙ የሴቶች መብት እንዲከበር ብሎም ሴቶችን በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በተለይም እናቶች በሥራ ቦታቸው ሀሳባቸው ሳይበታተን ልጆቻቸውን በቅርበት መንከባከብ የሚያስችላቸው የህጻናት ማቆያ መዕከል ከማዘጋጀት ጀምሮ ሌሎች ለሴቶች ምቹ የሥራ አከባቢ የሚፈጥሩ ስራዎች ይሰራሉ ሲሉ / ፅጌሬዳ ተናግረዋል፡፡

በስነ-ሥስርዓቱ "የራሳችን ጀግና ሴቶችን መዘከር እና ማክበር" በሚል ርዕስ የተለያዩ ጀግና ሴቶች የተዘከሩ ሲሆን በተለይም የሴቶች ተሳትፎና ሚና በአድዋ ጦርነት ምን ይመስል እንደነበረ በጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ገለጻ ቀርቧል፡፡

ዘንደሮ በኤጀንሲው የተከበረውን በዓል ልዩ የሚያደርገው በሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተቋሙ አባላት የማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሚያዋጡት ገንዘብ በቋሚነት ድጋፍ የሚደረግላቸው ግብረ ሰናይ ተቋማት በኤጀንሲው ቅጥር ግቢ መገኘታቸው ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ድጋፍ የሚደረግላቸው ተቋማት በኤጀንሲው ለሁለት ቀናት በሚቆየው አወደ-ርዕይ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሴት የተቋሙ አባላትም የተለያዩ የእጅ ሙያ እና የባልትና ሥራዎቻቸውን ይዘው እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንየሴቶችን መብት የሚያከብር ማህበረሰብ እንገባ!” በሚል መሪ ቃል በዓለም 110 በሀገራችን 45 ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

Most Viewed Assets