ኤጀንሲው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዲጂታል ሥርዓቶች ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጡ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ገለፀ

ኤጀንሲው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዲጂታል ሥርዓቶች ለሳይበር ጥቃት እንዳይጋለጡ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27/2013- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫው ሂደት የሚጠቀምባቸው የዲጂታል ግብዓቶችና የመረጃ ስርዓቶች በአገሪቱ የሳይበር ምህዳር ጥበቃ ውስጥ መካተታቸውን አስታወቀ።

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛው በሀገራዊው ምርጫ የሚሳተፉ ተቋማት የመረጃ መረብ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ኤጀንሲው ዝግጅት ማድረጉን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ዘንድሮ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሌሎች ሀገሮች ያጋጠሟቸው የሳይበር ጥቃቶች እንዳያጋጥም መከላከል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመረጃ ስርዓት በአገሪቱ የሳይበር ምህዳር ጥበቃ ውስጥ መካተቱን / ሹመቴ ግዛው ተናግረዋል።

የአገሪቱ የሳይበር ምህዳር ቢጠበቅም በምርጫው ላይ ሚና ያላቸው ተቋማት ትክክለኛውን አሰራር እየተከተሉ አለመሆኑና ብቁ የሰው ኃይል የሌላቸው በመሆኑ ራሳቸውን ለሳይበር ጥቃት ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ይህን ስጋት በመፈተሽ የሚጠቀማቸውን የቴክኖሎጂ ደህንነት አስቀድሞ የማረጋገጥ፣ ብቁና ስነ-ምግባር ያለው የሰው ሃይል የመመደብ፣ ውስጣዊ የሳይበር ደህንነት ፍተሻዎችን የማካሄድ ሙሉ ኃላፊነት አለበት ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል።

ኢዜአ ዋና ዳይሬክተሩን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው እንደ አገር በምርጫው ላይ ቀጥተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት የሳይበር ጥቃት እንዳይደርስባቸው ኤጀንሲው በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

ለዚህም 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚሠራየሳይበር ሬዲነስ ቲምተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

ቡድኑ ከዋና ስራው በተጨማሪ የሁኔታ ትንታኔዎችን እየሰራ ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ የማድረግ አገራዊ ተልዕኮ እንዳለውም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የተለያዩ ጥቃት አድራሾች በምርጫው ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራሮች እና የሌሎች ተቋማትን የመረጃ መረብ ጠልፈው ጉዳት እንዳያስከትሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ዶክተር ሹመቴ ገልጸዋል።

ኤጀንሲው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድንና የሌሎች ተቋማትን ውስጣዊ የቴክኖሎጂ አቅም እና የሰው ሃይል ብቃት ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በተቋማቱ ፍላጎት መሰረት ባለሙያ የመመደብ፣ ከስልጠና እስከ ቴክኖሎጂ ፍተሻ ተግባራትን የማከናወን እንዲሁም ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረጉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል።

Most Viewed Assets