በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረው የዲጂታል ፕሮፖጋንዳ

Nested Applications

Asset Publisher

"ያለንን አቅም አሰባስበን የሀገራችንን የሳይበር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ይገባል" የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

"ያለንን አቅም አሰባስበን የሀገራችንን የሳይበር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ይገባል" የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው Thu, 20 Jan 2022

የዲያስፖራው ተሳትፎ፣ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት!!

የዲያስፖራው ተሳትፎ፣ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት!! Sun, 16 Jan 2022

የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ!!

የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ!! Tue, 4 Jan 2022

ኤጀንሲዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በመረጃ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ኤጀንሲዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በመረጃ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ Tue, 28 Dec 2021

Asset Publisher

Asset Publisher

null በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረው የዲጂታል ፕሮፖጋንዳ

 

ዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ስንል ከኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ግኝትና መስፋፋት ጋር ተያይዞ የግለሰቦች፣ ድርጅቶች እንዲሁም አገራት የዕለት ከዕለት ነባራዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሳይበር ምህዳሩ የመግባታቸውን እውነታ ተከትሎ የሳይበር ምህዳሩ ተሳታፊዎችና ተጠቃሚዎች የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን የሚያስከብሩበት መንገድ ባህሪውን ከዲጂታል ምህዳሩ ጋር በማላመድ ማስተላለፍ እንደሚፈለጉት ጉዳይ ክብደትና ቅለት ሆን ተብሎ የሚሰራጩ መጠነ ሰፊ ሀሰተኛ መረጃዎችንና ምስሎችን እንዲሁም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የተለያዩ ጫናዎችን በጦርነት ወቅት፣ ከጦርነት በፊት እንዲሁም በድህረ-ጦርነት ጊዜ የኃይል ሚዛን የበላይነትን ለመቀዳጀትና ለማስጠበቅ የሚታለም የዘመኑ የመረጃ ጦርነት (information warfare) አካል ተደርጎ ይታሰባል፤

የዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ዓላማ ምንድን ነው? ከላይ በትርጓሜ ደረጃ እንደተመላከተው የዲጂታል ምህዳሩ ተዋንያኖች በሳይበር ቴክኖሎጂው ውስጥ መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያሰራጩበት የተለያዩ ዓላማዎች አሏቸው፤ ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡-

 • ተገቢ ባልሆነ መንገድ ተቀባይነትን ለማግኘት 
 • የመረጃ የበላይነትን ለማስጠበቅ
 • ኃይልን ለማጠናከርና የእፎይታ ጊዜን ለመግዛት
 • የተቀናቃኞችን ስም በማጥፋት በሀሰት መወንጀል እንዲሁም በተከታዮቻቸው ዘንድ አመኔታን ማሳጣት
 • ለአካላዊ ጦርነት ቅድመ-ዝግጅት ድጋፍን ለማሰባሰብና ተጨማሪ ኃይል ወይም ተከታይ ለማግኘት 
 • የስነ-ልቦና፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫናዎችን በመፍጠር ጦርነትን ማሸነፍ

የመረጃ ጦርነት የሚከናወንባቸው መንገዶች  

የመረጃ ጦርነት በተለያዩ መንገዶች ሊፈፀም ይችላል፤ ከነዚህም መካከል ዋነኞቹን ለመመልከት ያህል፡-

 • የስም ማጥፋት ዘመቻ፡- በመረጃ ጦርነት ውስጥ እንደዋነኛ የመቀናቀኛ መንገድ የሚቆጠረው የተቃራኒ ወገንን ስም በመጥፎ ማንሳት፣ ማጠልሸት እና ብዙሃኑም እንዲያምን እና ተፅእኖ እንዲፈጥር ማስቻል ነው።
 • ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፡- ሀሰተኛ መረጃዎችን እና ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በመፍጠር የተከሰቱ ሁነቶችን በማጋነን ወይም የተበዳይነት ስሜትን እጅግ በማጋነን የሚፈጠሩ እጅግ የተጠኑ እና የተቀነባበሩ እውነተኛ መስለው እንዲታመኑ ተደርገው በምስል፣ በተንቀሳቃሽ ምስል አሊያም በድምፅ የታገዙ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በተቃራኒ ወገን ላይ የመረጃ የበላይነት መውሰድ እና የብዙሃንን ድጋፍ ለማግኘት ትልቅ ጥረት ማድረግን ያጠቃልላል።
 • የተቃራኒ ወገንን መረጃ ማጣጣል እና ማስተባበል
 • የፈጠራ ውዥንብሮችን መፍጠር (hoaxing):-

ያልተፈጠሩ ሀሰተኛ ውዝንብሮችን በብዙሃኑ ዘንድ በተለያዩ መንገዶች በመንዛት የሰዎችን ትኩረት ማስቀየር፣ ስነልቦናዊ ጉዳት ማድረስ እና የሰዎችን እሳቤ መበዝበዝ እና በዚህም ክፍተት ተቃራኒ ወገንን ማጥቃት።

 • የሳይበር ጥቃቶችን መፈፀም፡- የመንግሥት ተቋማትንና የታወቂ ግለሰቦችን የማህበራዊ ትስስር ገጽ አካውንቶችንና ድረ-ገጾችን በመጥለፍ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን መለጠፍ።

ፕሮፖጋንዳ ከበላቸው ሀገራት ምን እንማራለን?

የሳይበር ምህዳር አብዮት በርካታ አገራትን ብሎም መንግሥታትን አንኮታኩቷል። አገራት እንዳልነበሩ ዜጎችም አገር እንደሌላቸው ለስደት ተዳርገዋል። በቱኒዚያ ታኅሣሥ 2010 ... የአረብ አብዮት የተጀመረው መሐመድ ቡአዚዚ፣ በአካባቢው ባለሥልጣናት (አረብ ስፕሪንግ) የደረሰበትን አያያዝ ለመቃወም ሲል ራሱን በእሳት ሲያቃጥል ነበር። ከዚያም የሳይበር ምህዳር አብዮት ወደ ግብፅ፣ የመንና ሊቢያ በመቀጣጠል ከመንግሥት ግልበጣ እስከ ከፍተኛ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሰብዓዊ ቀውሶች እንዲፈራረቁባቸው አድርጓል። የአብዮቱ ዓላማ መንግሥታትን ለማስወገድ አልሞ የተጀመረ ቢሆንም፤ የበርካታ አገራት ዜጎች ሕልም ግን እውን አልሆነም።

በፌስቡክና በትዊተር የተጀመረው የአረብ አብዮት ለየመን መጥፋት ብሎም የሊቢያን የቀደመ ከፍታዋን መቀመቅ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ጣልቃ በሚገቡ የአደጉ አገራት የሴራ አጀንዳ መሆኑን ከአብዮቱ ማግስት ለዓለም ግልፅ ሆኗል። የአብዮቱ መነሻ የዴሞክራሲ እጦት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ስር የሰደደ ጉቦ፣ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል፣ የሥራ አጥነት ቁጥር ብሎም የምግብ ዋጋ መጨመር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አበይት ጉዳዮች ናቸው። ዳሩ ግን የበሬ ወለደ የሳይበር ምህዳር ፕሮፖጋንዳ የሆስኒ ሙባረክ አገዛዝ እንዲፈርስ አድርጓል።

በዚህም የተነሳ በርካታ ግብፃውያን ለከፋ የኢኮኖሚ ግሽበት ችግር ተጋልጠው ነበር። ግብፅ የአገር ውስጥ እድገት በፈረንጆች 2009/2010 ከነበረው 5 ነጥብ 1 በመቶ ወደ 1 ነጥብ 6 በመቶ ማሽቆልቆል አጋጥሟታል። አምባገነን መንግሥት በሚል የአደጉ አገራት ትርክት የፈረሰችው ሊቢያ፣ ዜጎች የዜግነት ይከፈላቸው የነበረባት አገር ዛሬ እንደ ዜጋ ለመኖር በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተሰደው እንዲኖሩ፤ ለልመናም እጃቸው እንዲዘረጋ ተዳርገዋል። ስደትን አንፈልግም ያሉ ዜጎችም ሰብዓዊነታቸው እየተገፈፈ እንዲኖሩ ሆነዋል። ዜጎች ይህን ቀድመው ቢረዱ የሞአመር ጋዳፊ አስተዳደርን በፕሮፖጋንዳ አያፈርሱትም ነበር።

ዛሬ በአገራችን የተጀመረውን የዴሞክራሲ ጎዳና በርካታ የዓለም ሚዲያዎች፣ ግለሰቦች፣ የኢትዮጵያ እድገትና አንድነት ራስ ምታት የሆነባቸው አገራት ሳይቀሩ አሁን ያለውን መንግሥት አምባገነን የሚል ቅኔያቸውን ዜጎች እንዲሰሟቸው በእያንዳንዷ ቅፅበትና አጋጣሚ ፕሮፖጋንዳቸውን ሲያሰራጩ ውለው ያድራሉ። በዘመነ ቅኝ ግዛት ያልተገዛች የአፍሪካ መመኪያን በወሬ ወለደ ሊፈቷት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። አሜሪካ ኮሽ ባለበት ሁሉ እጇን እያስገባች እንደ አገር የቆሙ ሉዓላዊ አገራትን የወንበዴዎች ማማ እንዲሆኑ አድርጋለች። በአፍጋኒስታን የአሜሪካ ዱላና ፕሮፖጋንዳ 20 ዓመታት ዘልቆ አገሪቱን እንዳልነበር ማድረጓ አንዱ ማሳያ ነው። አሜሪካ በተለያዩ ባለስልጣኖቿ የአሸናፊነት ፕሮፖጋንዳዋን ብትነዛም አፍጋኒያውያንና ሕልማቸውን ከማቀጨጭ ውጭ ነፃነታቸውን ልትሰጣቸው አልቻለችም።

በሌላ በኩል በየመን የቀጠለው አብዮት በየመን ዘልቆ ከአገርነት ወደ ፍርስራሽነት ዜጎችም የስደት ሰለባ እንዲሆኑ ፕሮፖጋንዳና የአሜሪካ ለሳዑዲ መንግሥት የልቤን አስፈፅሚልኝ የፋይናንስ ድጋፍ ከፍተኛውን ሚና በመጫወቱ ከስምንት ዓመታት በላይ በዘለቀው የማያበራ ጦርነት የመን እንዳልነበር ሆናለች። ዛሬም አድጋለሁ ላለ አገር የማትተኛው አሜሪካ አገራችን በተደቀነባት ጊዜያዊ ችግር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ወታደራዊ ፕሮፖጋንዳዋን በበላይ ባለስልጣኖቿ ሳይቀር እየነዛች ይገኛል።

ለየመን መፍረስ የሳዑዲ፣ የኢራን፣ የአሜሪካና የመሰሎቿ ስውር ሴራና ደባ እንዳለበት በርካታ መረጃዎች ያመለክታሉ። ዛሬም የምሥራቅ አፍሪካ ታላቋና የአፍሪካ ኩራት የሆነችው አገር ኢትዮጵያ የእጅ አዙር ጦርነትና የፕሮፖጋንዳ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች። እንደ አሜሪካና ግብፅ ያሉ አገራት በይፋ በሚዲያዎቻቸውና በባለሥልጣኖቻቸው በኩል እናሸንፋለን እስከ ማለት ዘልቀዋል፤ አለፍ ሲሉም በከሰረ የፖለቲካ ጥቅም የታወሩ የእናት ጡት ነካሽ ፖለቲከኞችን ሳይቀር በመጠቀም ጊዚያዊና የሽግግር መንግሥት እናቋቁማለን የሚል ማህበር እስከመመስረት ዘልቀዋል። ዜጎች በማንነታቸው እንደሚገፉ አገራቸው ለእነሱ እንደማትጠቅማቸውም ሊነሱና ሊታገሉ ይገባል እያሉ ፕሮፖጋንዳቸውን ሲነዙ ይውላሉ፤ ያድራሉ።

በርካታ የአረብ አገራትን ከእድገት ማማ የመለሱ ሃያላን አገሮች ዛሬም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ካለሙት የእድገትና የዴሞክራሲ መሲህ ወደኋላ እንዲያሸበርኩ ብሎም የሚታዘዛቸውን አሻንጉሊት መንግሥት በመመስረት የአፍሪካውያን መመኪያ የሆነችውን አገር ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል። እናም በታሪክ ያልተፈታውን የጀግንነት ምስጢራችን በፕሮፖጋንዳና ዛቻ ብሎም በሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር አለፍ ሲልም እቀባ እጅ ሳንሰጥ ገብተው ካፈረሷቸው አገራት ተምረን በወሬ አገራችንና ትጥቃችን ሳንፈታ ዳግም ኢትዮጵያን ወደ ማማዋ ከፍ ልናደረጋት ብሎም ታላቋን አፍሪካን ለመገንባት ሀሞተ መራር መሆን ይጠበቅብናል።