አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Nested Applications

Asset Publisher

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተርን ተቀብለው አነጋገሩ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አለማቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት የአፍሪካ ዳይሬክተርን ተቀብለው አነጋገሩ Thu, 23 Mar 2023

ኢመደአ እና የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ኢመደአ እና የኢፌዲሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ Wed, 15 Mar 2023

ኢመደአ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ሶፍትዌር በማልማት ለሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስረከበ

ኢመደአ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ሶፍትዌር በማልማት ለሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስረከበ Fri, 3 Mar 2023

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ Wed, 1 Mar 2023

Asset Publisher

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡