ራሳችንን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል ልንወስዳቸዉ የሚገቡ የጥንቃቄ ርምጃዎች

Nested Applications

Asset Publisher

ኤጀንሲው ከአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ከሐረሪ ክልል ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ

ኤጀንሲው ከአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ከሐረሪ ክልል ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ Fri, 23 Jul 2021

ኤጀንሲው በ2013 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2014 መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

ኤጀንሲው በ2013 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2014 መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ Thu, 22 Jul 2021

ኢትዮጵያና እስራኤል የሳይበር ደህንነት ተቋም ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መከሩ

ኢትዮጵያና እስራኤል የሳይበር ደህንነት ተቋም ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መከሩ Thu, 22 Jul 2021

ኤጀንሲው ለፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ሃላፊዎች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ

ኤጀንሲው ለፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ሃላፊዎች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ Thu, 22 Jul 2021

Asset Publisher

Asset Publisher

News

 • ኤጀንሲው ለፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ሃላፊዎች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ Thu, 22 Jul 2021
ኤጀንሲው ለፋይናንስ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ሃላፊዎች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ
 • ኤጀንሲዉ ከተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸዉን የተቋሙን ድጋፍ ሰጪ አባላት አስመረቀ Fri, 25 Jun 2021
ኤጀንሲዉ ከተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸዉን የተቋሙን ድጋፍ ሰጪ አባላት አስመረቀ
 • ግብረሃይሉ ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረበ Wed, 23 Jun 2021
ግብረሃይሉ ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረበ

Asset Publisher

null ራሳችንን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል ልንወስዳቸዉ የሚገቡ የጥንቃቄ ርምጃዎች

 

 

የሳይበር ምህዳር ያልተማከለ፣ ባልታወቁ አካላት ሊንቀሳቀስ የሚችል፣ በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ የሆነ እና ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በሀገራት ደህንነት ፣ በሰብአዊ መብት፣ በግላዊነት Privac እና ሉዓላዊነት በሚባሉ የአንድ ሀገር ብሔራዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው።

በዚህም አለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለየ መልክ እየያዘች ከመምጣቷ ባሻገር የዕውቀትና የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡

የሳይበር ምህዳሩ የሰዉ ልጆችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ቀላል እና የኑሮ ዘይቤን በማዘመን ደረጃ ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ የሳይበር ምህዳሩ ከፈጠራቸዉ መልካም ዕድሎች ጎን ለጎን የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ይዞ መጥቷል፡፡

እነዚህን ስጋቶች ተቋቁሞ በምህዳሩ ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች እና እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም ሊወሰዱ ከሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

 1. ጠንካራ የሆነ የይለፍ ቃል (Password) መጠቀም፡- በ2011 ዓ/ም ኢመደኤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ባደረገዉ አንድ ጥናት 69.9 ከመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ሥለ ጠንካራ የይለፍ-ቃል (Password) ምንነት ግንዛቤ እንደሌላቸዉ ያሳያል፡፡ ጠንካራ የይለፍ-ቃል (የቁጥር፣ የፊደላትና የምልክቶች ጥምር) የሆነ የይለፍ-ቃል መጠቀም፣ ነባሪ (Default) የይለፍ-ቃሎችን በፍጹም አለመጠቀም እና የይለፍ-ቃሎቻችንን ለማንም አለማጋራት ነው ፡፡
 2. ትክክለኛ ፀረ-ቫይረስ መጠቀም፡- ለኮምፒዉተሮቻችን፣ ስልኮቻችን እና መሰል ከኢንተርኔት ጋር ለተቆራኙ ቁሶች ፀረ-ቫይረስ መጠቀም እንዲሁም ሌሎች አጥፊ ሶፍትዌሮችን ደህንነት የማስጠበቂያ አማራጮችን መተግበር፡፡
 3. የሚጠቀሙበትን ኮምፒዉተር/ስማርት ስልክ እና መሰል ከኢንተርኔት የተቆራኙ ቁሶችን ኦፕሬቲንግ ሲስተም (Operating Systems) ማዘመን፡፡
 4. መረጃዎችን መመስጠር፡- በስርዓተ ኮምፒዉተር ፣ በስልኮቻችን እንዲሁም በሌሎች መረጃ ቋቶች ተከማችተዉ የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን መመስጠር (Encrypted)
 5. ቀሪ መያዝ(Backup) መጠቀም፡- አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎቻችንን ግልባጭ (Backup) መያዝ፡፡
 6. የምንጎበኘዉን ድረ-ገፅ ትክክለኛነት ማረጋገጥና ሊንኮችን ስንጠቀም መጠንቀቅ፡- የምንከፍተውን ድረ-ገጽ ዩአርኤል URL በጥንቃቄ መመልከት እና ትክክለኛነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር በኢ-ሜይልና በተለያዩ መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎች የሚላኩ ሊንኮችን (አባሪዎችን) በጥንቃቄ መመርመር እና ትክክለኛነታቸዉን ማረጋገጥ፡፡
 7. አፕሊኬሽኖችን እና ሶፍትዌሮችን ከትክክለኛዉ ቋት ማዉረድ (download) መተግበሪዎች ወይም ሶፍትዌሮችን ስናወርድ የተጠቀምነዉ የሶፍትዌር እና የአፕሊኬሽን ቋት ህጋዊና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
 8. ለማህበራዊ ሚድያ አካዉንቶች ባለሁለት ደረጃ የትክክለኛነት ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication) መጠቀም፡- የማህበራዊ ሚዲያዎች ስንጠቀም ጠንካራ የይለፍ-ቃል ከመጠቀም በተጨማሪም ባለሁለት ደረጃ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ተግባራዊ ማድረግ መቻል ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም የማንኛዉንም አገልግሎት ተጠቅመን ስንጨርስ በመጨረሻ ሎግ አዉት (Logout) ወይም ሳይን አዉት (Sign out) ማድረጋችንን አለመዘንጋት
 9. ነፃ የህዝብ ዋይፋይ ስንጠቀም መጠንቀቅ፡- የተለያዩ ነፃ ፐብሊክ ዋይፋዮችን ለኢንተርኔት ግንኙነት በምንጠቀምበት ጊዜ ለአደጋ ተጋላጭ የምንሆንበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ ከተቻለ ከመጠቀም መቆጠብ ካልሆነም ሚስጥራዊና እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችን በህዝብ ዋይፋይ ከመጠቀም መቆጠብ፡፡ ከዛ ይልቅ ዴታ መጠቀም፡፡
 10. _ከማህበራዊ ምህንድስና ማጭበርበርያ ዘዴዎች መጠንቀቅ፡- የማህበራዊ ምህንድስና የማጭበርበሪያ ዘዴዎች የምንላቸዉ የሰዉ ልጆችን ስነ-ልቦና መሰረት ያደረጉና ሲስተሞችን በሀይል ሰብሮ ከመግባት ይልቅ በዘዴ ማታለልን አማራጭ በማድረግ መረጃዎችን ለመድረስ የሚዉል የሳይበር ጥቃት ዓይነት ነዉ፡፡

እርስዎም የሳይበር ምህዳሩ ከፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ ባሻገር እጅግ ዉስብስብ እና አደገኛ መሆኑን በመረዳት ከላይ የቀረቡትን የጥንቃቄ ርምጃዎች በመተግበር በራስዎ፣ በተቋምዎ እንዲሁም በሀገር ላይ ሊደርስ የሚችልን የሳይበር ጥቃት ይከላከሉ፡፡

Asset Publisher