ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ

Nested Applications

Asset Publisher

ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች የአመራርነት ጥበብ ሥልጠና ተሠጠ

ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች የአመራርነት ጥበብ ሥልጠና ተሠጠ Thu, 4 Mar 2021

የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ልዑክ በኢመደኤ የስራ ጉብኝት አደረገ

የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ልዑክ በኢመደኤ የስራ ጉብኝት አደረገ Thu, 18 Feb 2021

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ Wed, 3 Feb 2021

የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ

የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ Wed, 27 Jan 2021

Asset Publisher

Asset Publisher

null ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ

 

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ በመገኘት የመስክ ጉብኝት እና የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ጉብኝቱ ተቋሙ ያስገነባውን አዲስ ህንጻ ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን ኤጀንሲው የሥራ ክፍሎቹን ለሠራተኞች ምቹ በሆነና እና ዘመናዊ አደረጃጀትን በተከተለ መንገድ እያደረጃ የለበትን መንገድ ተመልክተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ተቋሙ በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን አፈጻጸም ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸው የተቋሙን አዲሱን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት መስኮች፣ የበጀት አጠቃቀም፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም ለወቅታዊ ጉዳዮች ምላሽ መስጠት ላይ ኤጀንሲው ያከናወናቸውን ተግባራትን በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከትሎ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን የተቃጡ ሲሆን በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ 6 ወራት ተፈጽሞ ከነበሩ ጥቃቶች በዚህኛው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከእጥፍ በላይ የሆነ የሳይበር ጥቃቶች መፈፀማቸውን ዋና ይይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ ለህንጻ ኪራይ በዓመት ሲያወጣ የነበረውን 87 ሚሊዮን ብር ወጪ ለመሳቀረት በወሰደው ቁርጠኛ ውሳኔ ሲያስገነባ የነበረው አዲስ ህንጻ ሳይጠናቀቅ ሠራተኞችን ይዞ በመግባትና ህንጻውንም በቅርበት በመከታተል ከፍተኛ የመንግስት ወጪን ማዳን መቻሉን ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል፡፡

ከበጀት አጠቃቀም አኳያም ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ጅማሬ በርካታ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም ህግና ህግን መሠረት ባደረገ አግባብ ተፈጻሚ እንዲሆን ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለወቅታዊ ጉዳይ ምላሽ መስጠት በተመለከተም ኤጀንሲው የኮቪድ -19 ወረርሽኝን እንደሀገር ለመከላከል በተወሰዱ እርምጃዎች በርካታ አበርክቶዎችን ማከናወኑን፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሊት ክንውንን ለማስተጓጎል የተፈጸሙ ጥቃቶች ማክሸፍ መቻሉን እና በሰሜን የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው የህግ ማስከበር እርምጃ የተቃጡ በርካታ ጥቃቶችን አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ መቆጣጠር መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በነዚህን ሥራዎች ኤጀንሲው በውጤታማነት ማከናወን በመቻሉ እንደሀገር ሊከሰቱ ይችሉ የነበሩ መጠነ ሰፊ ኪሳራዎችን ኤጀንሲው መታደግ መቻሉን ዶ/ር ሹመቴ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርት የቀረቡለትን እና በመስክ ጉብኝት የተመለከታቸውን ጉዳዮች መሰረት በማድረግ አስተያየቶችን ሰጥቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ በጉብኝታቸው መደሰታቸውን እና ኤጀንሲው በአንድ በኩል ተቋም በመገንባት ተጠምዶ በሌላ በኩል በሀገር ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከል ሲያደርግ የነበረው ተግባር ለሌሎች ተቋማትም በአርዓያነት የሚገለፅ ሥራ በመሆኑ ኤጀንሲው ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡፡

በተለይም ተቋሙ ለታዳጊዎች ትኩረት በመስጠት የታዳጊዎች የሳይበር ተሰጥኦ ማጎልበቻ ማዕከል ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማዘጋጀቱ በእጅጉ ሊያስመሰግነው የሚገባ ተግባር መሆኑን ዶ/ር ነገሬ ገልጸዋል፡፡

በተላከዉን ሪፖርት ልክ መሰራቱን ማየት አለብን ብለን ብለን ብንመጣም በመስክ ምልከታ ወቅት አስቀድመን በሪፖርት ከተቀመጠዉ እና ከገመትነው በላይ ስራዉ እየተሠራ መሆኑን ለመታዘብ የቻልንበት ነው ሲሉ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

ሌሎች የቋሚ ኮሚቴ አባላትም በጉብኝቱ በጣም መርካታቸውን ገልጸው ኤጀንሲው በሠራው ልክ በአግባቡ በላከልን ሪፖርት ላይ አለመገለፁን ተናግረዋል፡፡

በተለይም ኤጀንሲው ለሰው ሀብት ልማት የሰጠው ትኩረት፣ ተቋሙ የሥራ አከባቢውን ማራኪና ምቹ እንዲሆን እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሠራር የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረው የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ኢመደኤ የተወጣው ሚናም ከፍተኛ በመሆኑ እውቅና ሊሰጠው የሚገባ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ተቋሙ እየሠራቸው ያሉ በርካታ ሥራዎች በጣም የሚያስመሰግኑ እና ለሌሎች ተቋማትም ተሞክሮ የሚሆኑ በመሆኑ ሊበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ተቋሙ ይበልጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት ሊያጠናክር፤ የተሰሩ ፕሮጀክቶች ወደ መሬት መውረዳቸውን ሊከታተል፤ ሠራተኞችን የሚያበረታቱ የማበረታቻ ሥርዓቶች ሊዘረጋ እና የበጀት አጠቃቀሙንም የበለጠ በማሻሻል አፈጻጸሙን ሊያሳድግ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher