ወቅታዊ የሃገራችንን ሁኔታ ምክንያት በማድረግ ከኢመደኤ የተሰጠ የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ ማሳሰቢያ
Nested Applications
Asset Publisher
አዲስ አበባ፦ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም:- በሃገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ከምንግዜውም በላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዝግጁ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
ሆኖም ሁሉም የበይነ-መረብ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ሕብረተሰቡ ሊከሰቱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን በንቃት በመከታተል የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ ኤጀንሲው ያሳስባል፡፡
በተለይም ቁልፍ የሃገራችን ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን (የፋይናንስ፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የልማት ድርጅቶች እንዲሁም መሰል ተቋማትን) ዒላማ ያደረጉ የሳይበር ጥቃቶች ሊሰነዘሩ የሚችል በመሆኑ ተቋማቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው ያስታውቃል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተቋማትም ይሁኑ ህብረተሰቡ ማናቸውም አይነት የሳይበር ጥቃት ሙከራም ሆነ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ከዚህ በታች በተገለጹት አድራሻዎች በማንኛውም ሰአት በፍጥነት ጥቆማ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ስልክ፡ +251 936825343, +251 944336802, +251 900896448
ኢ-ሜይል፡ ethiocert@insa.gov.et
ነጻ የስልክ መስመር፡ 933