ኤጀንሲው በሀገሪቱ እያደገ የመጣዉን የዲጂታል ስርዓት እድገት በሚመጥን መልኩ የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ አደረገ

Nested Applications

Asset Publisher

ኤጀንሲው የህጻናት፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገጸ

ኤጀንሲው የህጻናት፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገጸ Wed, 2 Dec 2020

አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ

አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ Tue, 24 Nov 2020

የኤጀንሲው አመራርና አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገለፁ

የኤጀንሲው አመራርና አባላት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ገለፁ Tue, 17 Nov 2020

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ Mon, 9 Nov 2020

Asset Publisher

Asset Publisher

null ኤጀንሲው በሀገሪቱ እያደገ የመጣዉን የዲጂታል ስርዓት እድገት በሚመጥን መልኩ የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ አደረገ

 

አዲስ አበባ ጥቅምት 3/2013፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በሀገሪቱ እያደገ የመጣዉን የዲጂታል ስርዓት እድገት የሚመጥን እና በአስተማማኝ ሁኔታ ሃገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችል የ 5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ በኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ይፋ ተደርጓል፡፡

ኤጀንሲዉ የኢንፎርሜሽን የበላይነትን በማረጋገጥ ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚያስችል ተወዳዳሪና የማይበገር የኢንፎርሜሽን ደህንነት አቅም እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ስትራቴጂክ እቅዱ ተዘጋጅቷል፡፡

በዚህም ኤጀንሲዉ የአምስት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዉን በኢኮኖሚ፣ በፓለቲካ እና ፣ በሳይበር ስነ-ምህዳር ውስጥ ሃገሪቱ ብቁ ተዋናይ እንድትሆን በሚያስችል መልኩ እቅዱ መዘጋጀቱን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በስትራቴጂክ ዕቅዱ አዳዲስ የሳይበር ደህንነት እይታዎችን፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጅማሮ፣ ሀገሪቱ ያለችበትን የጂኦ-ፓለቲካ ተግዳሮቶችን እና የወቅቱን ዓለም አቀፍ የሳይበር ምህዳር ዕድገት ታሳቢ ባደረገ አግባብ መቃኘቱን ዶ/ር ሹመቴ አብራርተዋል ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች በየጊዜዉ እየጨመሩ መምጣታቸውን ያነሱት ሃላፊዉ በተመሳሳይ በሃገራችንም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሳይበር ጥቃቶች መበራከታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማሳያነት ባለፈዉ ዓመት ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የፋይናንስ፣ የሚዲያ እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች በሃገሪቱ ያሉ ወሳኝ መሰረተ-ልማቶችን ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መቃጣታቸዉን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ የሳይበር ጥቃት ሙከራዉን ኤጀንሲው ማክሸፋን አስረድተዋል፡፡

የሳይበሩን አለም ደህንነት ማስጠበቅ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው አለመሆኑን የጠቆሙት ሃላፊዉ ከዚህ በኋላ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከግለሰብ ጀምሮ ግዙፍ የመረጃ ቋቶችን የሚያንቀሳቅሱ የግልና የመንግስት ተቋማት በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ኤጀንሲዉ በተናጠል ያከናዉን የነበረውን የሃገሪቱን የሳይበር ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር በማሻሻል ሌሎች የትምህርት፣ የሚዲያ፣ እና የፋይናንስ ተቋማት የራሳቸውን አቅም የመገንባት ስራ እንደሚከናወን ዶ/ር ሹመት ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲዉ አሁን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ፣ ወደፊት የሚደርስበትን አቅጣጫ እና የተከለሰውን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ ቀድሞ ይጠቀምበት የነበረውን ሎጎ መቀየሩን ዋና ዳይሬክተሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

ኤጀንሲዉ የተደረገዉ ሪፎርም በሀገሪቱ ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅምን ከመፍጠር ባሻገር የመቆጣጠር እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አጸፋዊ ምለሽ መስጠት የሚያስችል የዝግጁነት ቁመና እንደፈጠረ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አብራርተዋል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher