ኤጀንሲው የግብር ስርዓትን ቀልጣፋ የሚያደርግ የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

Nested Applications

Asset Publisher

ኢመደኤ ከኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ኢመደኤ ከኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ Fri, 11 Jun 2021

ኤጀንሲው የግብር ስርዓትን ቀልጣፋ የሚያደርግ የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ኤጀንሲው የግብር ስርዓትን ቀልጣፋ የሚያደርግ የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ Thu, 10 Jun 2021

መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ከመከላከል ባለፈ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የንቃተ- ህሊና ክፍተት ሊሞሉ ይገባል ተባለ

መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ከመከላከል ባለፈ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የንቃተ- ህሊና ክፍተት ሊሞሉ ይገባል ተባለ Thu, 3 Jun 2021

ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ

ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ Wed, 2 Jun 2021

Asset Publisher

null ኤጀንሲው የግብር ስርዓትን ቀልጣፋ የሚያደርግ የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከባንኮች ጋር የኢ-ታክስ ስርዓትን ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር የሚያስችለውን የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛው በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ "ደራሽ ፕላትፎርም" በኤጀንሲው የበለጸገና መረጃዎችን በአንድ ቋት በመሰብሰብ የመረጃዎቹን ደህንነት በመሰረታዊነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለሀገሪቱ የጀርባ አጥንት የሆነዉን የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ከግብር ከፋዮች ጋር ለማስተሳሰር እና የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ የተዘጋጀውን ቴክኖሎጂ ሙሉ ለሙሉ መተግበርና ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባ ጥቅም እንዳይታጣ የሚያግዝ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉ / ሹመቴ ግዛዉ አሳስበዋል፡፡

የግለሰቦች፣ የተቋማት እንዲሁም የሀገሪቱ የመረጃ ደህንነት መጠበቅ ሃላፊነት በኤጀንሲው ላይ የተጣለ በመሆኑ ደህንነቱን የማረጋገጥ ስራ በኢመደኤ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የሳይበር ጥቃት አድራሾች ዋና ዒላማ የፋይናንስ ተቋማት መሆናቸውን ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህ የመረጃ መንታፊዎች ትኩረት የሚያደርጉት ገንዘብ ላይ በመሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ደህንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ስራዎችን መስራት ይጠይቃልም ብለዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ አፈጻጸም ሚንስትር ደኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ በበኩላቸው ጊዜዉ ተቋማት ዉጤታማ እና ጥሩ አገልግሎት ለመስጠት በራቸዉን ሳይዘጉ አሰራሮቻቸዉን ለተጠቃሚዎቻቸው ግልጽ የሚያደርጉበትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጥምረት መስራት የግድ የሚልበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍም የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አሰባሰብ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል ሲሉ ሚንስትር ደኤታው ጠቁመዋል፡፡

በዚህም በኢመደኤ የበለጸገው የደራሽ ፕላትፎርምን ከባንኮች ጋር በማገናኘት የግብር ከፋዮችን የግብር ክፍያ በኢ-ታክስ አማካኝነት በወቅቱ ለመሰብሰብ እንደሚያግዝ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የገቢዎች ሚንስቴር የህግ ተገዥነት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ይህን አሰራር በሀገሪቱ ዉስጥ ካሉ ሁሉም ባንኮች ጋር መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን አሰራሩ ከፌዴራል ግብር ከፋዮች ወደ ክልል የሚወርድበትን ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ይህ ስርዓት ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ የተያዘ ነዉ ያሉት አቶ ዘመዴ ምክንያቱ ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ቴክኖሎጂዉን ከማልማት ባሻገር ደህንነቱን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህ የመግባቢያ ሰምምነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጨማሪ ዳሽን ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ህብረት ባንክ እና ብርሃን ባንክ በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡

Asset Publisher

News

  • ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ Wed, 2 Jun 2021
ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ
  • በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ Wed, 2 Jun 2021
በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ
  • ከፍተኛ ገቢ በመሰብሰብ ለሽብር ተልዕኮ እያዋሉ ባሉ የሽብርተኛው ህወሓት እና ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የንብረት እግድ ተጣለ Tue, 1 Jun 2021
ከፍተኛ ገቢ በመሰብሰብ ለሽብር ተልዕኮ እያዋሉ ባሉ የሽብርተኛው ህወሓት እና ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የንብረት እግድ ተጣለ

Asset Publisher

Asset Publisher