የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ልዑክ በኢመደኤ የስራ ጉብኝት አደረገ
Nested Applications
Asset Publisher
Asset Publisher
በደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር የተመራ የደቡብ ሱዳን የልዑካን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በመገኘት የስራ ጉብኝት እና ከተቋሙ የበላይ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
ውይይቱ በዋናነት ሁለቱ ሃገራት በኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ስታገኝ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ እንደነበር ያወሱት የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር፤ አሁንም ቢሆን ደቡብ ሱዳን የተጠናከረ የሳይበር ደህንነት ተቋም እንዲኖራት በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዋል፡፡
የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው የደቡብ ሱዳንን የኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነት በማጠናከር ረገድ በዋናነት በሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች፤ ማለትም በሠው ሃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማት እና በአሰራር ሥርአት ዝርጋታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ሃገራዊም ይሁን ቀጠናዊ የኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነትን ለማርገጋጥ ሃገራት በጋራና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በውይይቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡