የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
Nested Applications
Asset Publisher
Asset Publisher
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ደህንነቱ የተጠበቀ ዳታ ሴንተር ለመገንባት በሚያስችለው ሂደት ውስጥ የማማከር ስራን ለማከናወን የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
በፊርማ ስነ ሥርአቱ የተገኙት የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ራሱን ለማዘመን እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ኤጀንሲው የተሰጠውን የማማከር ሃላፊነት በቁርጠኝነት እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ኤጀንሲው ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ አውስተው የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትም ቁልፍ የመንግስት ልማት ተቋም እንደመሆኑ ያለበትን የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ለመቅረፍ ኢመደኤ ከፍተኛ ሃለፊነት ወስዶ ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ መሀሩ በበኩላቸው ኢመደኤ በዘርፉ በቂ ልምድ ያለው በመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ ዳታ ሴንተር ለመገንባት በምናደርገው ጥረት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ተቋማችን የሚያስገነባው ዳታ ሴንተር ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር ከፍተኛ የእውቀት ሽግግር እንዲኖር የሚደረግበት ነው ብለዋል።
የማማከር ስራው አንድ አመት ከስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን ከዳታ ሴንተሩ ግንባታ ጀማሮ እስከ የደህንነት ፍተሻ ድረስ እንደሚዘልቅ በስነ ሥርአቱ ተነግሯል።