ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ

Nested Applications

Asset Publisher

null ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ

 

የጋራ ሃላፊነት ለሳይበር ደህንነትበሚል መሪ ቃል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር የሚዲያ ሳይበር ተጋላጭነት ኮንፍረንስ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በሥነ-ስርዓቱ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር / ሹመቴ ግዛዉ በአሁኑ ጊዜ ዓለም በሳይበር ምህዳር አማካይነት አንድ መንደር በሆነችበት በዚህ ዘመን የሳይበር ሀይል ከማናቸውም ብሔራዊ አቅሞች በላይ ቁልፍ የመወዳደሪያ መድረክ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የሳይበር ምህዳሩ የራሱ የሆኑ መልካም እድሎችን የፈጠረውን ያህል በአንጻሩ ምህዳሩ እያደረሰዉ ካለዉ ጉዳት አንጻር በያዝነው የፈረንጆቹ 2021 አለም በሳይበር ጥቃት ብቻ እስከ 6 ትሪሊየን ዶላር ልታጣ እንደምትችል / ሹመቴ ገልጸዋል፡፡ ይህም አሀዝ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ 2025 እስከ 10 ትሪሊየን ዶላር ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታን ስናይ የሳይበር ደህንነት ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጋረጠባት ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣዩ ሰኔ ወር ከሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ እና ከሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ ስኬታችን በማይዋጥላቸው አንዳንድ አካላት የሳይበር ጥቃት ለመፈጸም ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ ነዉ ያሉት / ሹመቴ በሀገራችን የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንም ስራቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የሚሰጡትን ትኩረት ያህል የቴክኖሎጂውን ደህንነት ለመጠበቅና ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት እጅግ አነስተኛ እንደሆነ አዉስተዋል፡፡ ይህም በሳይበር ጥቃት የሚደርሱ አደጋዎች ጉዳት የከፋ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ኢድሪስ በበኩላቸዉ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን እና ከእነዚህ በፍተኛ ደረጃ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ዘርፎች መካከል የሚዲያ ተቋማት ግንባር ቀደም መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንት ኤጀንሲ ጋር በጋራ መስራት መቻላችን በሀገራችን ከምርጫ እና ከሚዲያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል አጋዥ መሆኑን አቶ መሃመድ እድሪስ ጠቁመዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይየሳይበር ደህንነት እና የመገናኛ ብዙሃን ሚናበሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ Wed, 2 Jun 2021
ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑት መካከል የሚዲያ ዘርፍ አንዱ መሆኑ ተገለጸ
  • በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ Wed, 2 Jun 2021
በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ
  • ከፍተኛ ገቢ በመሰብሰብ ለሽብር ተልዕኮ እያዋሉ ባሉ የሽብርተኛው ህወሓት እና ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የንብረት እግድ ተጣለ Tue, 1 Jun 2021
ከፍተኛ ገቢ በመሰብሰብ ለሽብር ተልዕኮ እያዋሉ ባሉ የሽብርተኛው ህወሓት እና ሸኔ ቡድን አባላት ላይ የንብረት እግድ ተጣለ

Asset Publisher

Asset Publisher