የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መ/ቤት ህንጻ ምረቃን አስመልክቶ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በምረቃ ስነስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል

Nested Applications

Asset Publisher

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መ/ቤት ህንጻ ምረቃን አስመልክቶ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በምረቃ ስነስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል

 

 

ክቡር የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ፡ የእለቱ የክብር እንግዳ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ጠንሳሽና ባለራእይ

ከቡራን ሚኒስትሮች

ክቡራን ጥሪ የተደረገላቸሁ እንግዶች

ክቡራን የበአሉ ታዳሚዎች

ክቡራንና ክቡራት

በቅድሚያ ላለፉት 13 አመታት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሰራ ቦታ ባለቤትነት ህልም ተፈትቶ ለበርካታ አመታት ከነበረበት የቢሮ ተከራይነት ሰቀቀን ወጥትን የራሳችን የሆነ ግዙፍና ዘመናዊ የሕንጻ ባለቤት በመሆናችን መላውን የተቋማችንን ተገልጋዮች፣ የኤጀንሲያችንን ማህበረሰብ እንዲሁም በሕንጻው ግንባታ ሂደት ከጥንስስ ጀምሮ እስከዛሬዋ እለት ድረስ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ተቋማትና ግለሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ፤ እንኳን ደስ ያለን፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከምስረታው ጀምሮ በርካታ የኪራይ ሕንጻዎችን ተጠቅሟል፤ አቀያይሯል፡፡ ከአንዱ የኪራይ ሕንጻ ወደ ሌላው በሚደረግ የዝውውር ሂደት በርካታ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፏል፡፡ የኤጀንሲውን ተልዕኮ ታሳቢ ያደረገ የኪራይ ሕንጻ ለማግኘት የነበሩት ተግዳሮቶች፣ በሕንጻ ቅያሬ ወቅት በቢሮ ቁሳቁሶች ላይ ይደርስ የነበረው እንግልትና ጉዳት ፣ የኤጀንሲው ቢሮ በተቀየረ ቁጥር የተቋሙ አባላትም የመኖሪያ ሰፈራቸውን በመቀየር ያሳለፉት ውጣ ውረድና አለመረጋጋት፤ እንዲሁም ለቢሮ ኪራይ በሚል የተተጋነነ የገንዘብ መጠን የማይረሱ ትውስታዎች ናችው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ ኤጀንሲው ያለፈባቸውን ውጣ-ውረዶች አብራችሁ ያሳለፋችሁ ሠራተኞቻችን፤ እነሆ የራሳችሁ ሕንጻ ተገንበቶ ተጠናቋልና፤ ዛሬ ቤት ለእንቦሳ ብቻ ሳይሆን ቤት ለኢንሳ ተብላችኋል፡፡ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡

ክቡር ጠ/ሚ፤ ክቡራትና ክቡራን

በአብዛኛው በሃገራችን የመንግስት ህንፃዎች ግንባታቸው ሲጀመር ይጠናቀቃሉ ተብለው በታቀደላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቅ መንግስትን ለከፍተኛ ወጪ ሲዳርጉት ይስተዋላሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክትም ይሄው ዕጣ ፋንታ ከገጠማቸው አንዱ የነበረ ቢሆንም፤ በሃገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት የሰጠውን ፈጣን ውሳኔና ጅምር ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማስጨረስ አቅጣጫን በመከተል በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መ/ቤት ህንፃ ታላላቅ ከሚባሉት የመንግስት የግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ እንደመሆኑ መጠን የግንባታው መጠናቀቅ ኤጀንሲውን ጨምሮ ህንጻዎቹን የሚጠቀሙባቸው ተቋማት ማለትም ሰላም ሚኒስቴር፤ የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ማእከል እና የፋይናንስ ኢንተለጀንስ ማእከል በየአመቱ ለህንጻ ኪራይ መንግስት ሲከፍል የነበረውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት ለሌሎች ሃገራዊ የልማት ስራዎች ገንዘቡን እንዲያውል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ብቻ እንኳን ብንወስድ በአመት 87 ሚሊየን ብር ላለፉት በርካታ አመታት ወጪ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ከሕንጻ ኪራይ ባርነት ነጻ መውጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የዚህን ግንባታ ሰራ አጓታች ምክንያቶችን ለይቶና ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ በርካታ እልህ አስጨራሽ ወራቶችን አሳልፈናል፡፡

በዚህም ምክንያት ፍጥነት፤ ውጤትና ጥራት እርስ በርሳችው እየተጋጩ ከፍተኛ ፍልሚያ ውስጥ ገብተው እንደነበር የማይረሳ ተውስታችን ነው፡፡ ፍጥነት፤ ውጤትና ጥራት ሶስቱም ያስፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ሶስቱንም አብሮ ማስኬድ ፈታኝና ትልቅ ጥበብን የሚጠይቅ የትግል ሜዳ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህም ከፍተኛ የትንቅንቅ ወቅት በአማካኝ በሶስት አመታት ውስጥ ሊሰሩ የነበሩትን ስራዎች በስድስት ወራት ገዜ ውስጥ ሰርትን ማጠናቀቅ መቻላችን በፕሮጀክቱ የግንባታ ታሪክ ውስጥ ወርቃማ ምዕራፍ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ክቡር ጠ/ሚ፤ ክቡራትና ክቡራን

ታዲያ በዚህ ወርቃማ ምዕራፍ ዉስጥ ከዚህ ውጤት መገኘት ጀርባ የ MH engineering አማካሪ ድርጅት መፍተሄ ተኮር መሆን፤ የ Defense Construction Enterprise የወቅቱ አመራሮች ቁርጠኝነት፤ የፌደራል መንግስት ቢሮዎች ግንባታ ፐሮጀክት ጽ/ቤት አገናዛቢነት፤ የሰላም ሚኒስቴር ክትትልና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የ 24/7 ፍልስፍናውን ተግባራዊ ማድረግና ዙር አክራሪነት ጎልተው የሚጠቅሱ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሮጀከቱ መጠናቀቅ የሰጡት ትኩረትና አመራር የመስፍንጠሪያ አለት ሆኖን ለድል በቅተናል፡፡

ክቡር ጠ/ሚ፤ ክብራንና ክቡራት

ከአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት መፈጠር ጋር ተያይዞ አለም በከፈተኛ ፍጥነት ከአካላዊነት ወደ ዲጂታል ስነምህዳር እየተቀየረች፤ ዜግነት በተገባር ዲጂታል እየሆነ፤ ጦርነት በ Virus, Spyware, Malware, Ransomware, Geoint, EW ወዘተ እየሆነ በሚሄድበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያም የጦርነት ውሎዎች እንደስከዛሬው ጉራ፤ ጉንደት፤ አድዋ፤ ባድመ፤ ካራማራ፤ ወዘተ... ብቻ ሳይሆን አዳዲስ የሳይበር ጦር ሜዳ ዉሎዎች በ Ethio-CERT, EW እና በሌሎቸ ተያያዥ የዲጂታል ሜዳዎች ላይ እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ መናገር የምፍልገው በዚህ ውቅት ከየትኛዉም አቅጣጫ ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከተና ካስፈለገም መልሶ ለማጥቃት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዝግጅት የተደረገ መሆኑን ነው፡፡

ስለዚህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳየበር ምህዳሩን አለም አቀፍ ተዋናኞች ግምት ወስጥ በማስገባት፤ የኢትዮጰያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እውን መሆን ታሳቢ በማድረግ፤ የ ሃገሪቱን NATIONAL CYBER SECURITY INDEX ለማሻሻል የቴክኖሎጂና የዕውቀት ባለቤት መሆንን ጨምሮ አምስት የትኩረት መስኮችን ለይቶ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በያዝነው አመት የተጀመረውና በስፋት ተጥናክሮ የሚቀጥለው የዘርፉ Product Development and Commercialization የተሰኘው አዲሱ Initiative ወይም ጅማሮ ተጠቃሽ የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎቻችን አካል ነው፡፡ በቅርቡ ስራዉን የጀመረውና የተቋሙን ወድፊታዊነት አመላካች የሆነው የ ኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕክልም ለዘርፉ አዲስ ተስፋን ሰንቋል፡፡

ታዲያ እነዚህን ሁሉ ስራዎች በአግባቡ ለመከወን የእውቅትና የቴክኖሎጂ ባላቤትነት ብቻ ሳይሆን የስራ ቦታ ባለቤትነትም ወሳኝ በመሆኑ እነሆ ዛሬ እንደሃገራችን አገርኛ አባባል “ፈርሱም ይሄው ሜዳውም ይሄው” ሆኖለናል፡፡

ክቡር ጠ/ሚ፤ ክቡራትና ክቡራን

ይህ ዛሬ የሚመረቀው ዋና መ/ቤት የግንባታው ስራ ተቋራጭ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ MH Engineering አማካሪ ድርጅት እና መንግስት ደግሞ በከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የፌደራል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ ቤ/ት አማካኝንት ፋይናንስ አድርጎታል፡፡

የፕሮጀክቱ ወጪ 2.33 ቢሊዮን ብር ገደማ ሲሆን አጠቃላይ የግቢው ስፋት 21,371.2 ካ.ሜ ነው ፡፡ ሕንጻው ያረፈበት ቦታ ስፋት 7,550 ካ.ሜ ሲሆን ሰድስት እርስ በርሳችወ የተያያዙ ህንጻዎች እና ሶስት የሴኪውሪቲ ክሊራንስና መግቢያዎችን በተጨማሪነት ይዟል፡፡ የህንጻዎቹ ርዝማኔም 4ቱ ህንጻች እያንዳንዳቸው ባለ 14 ወለሎች፤ አንዱና መካከለኛው ህንጻ ባለ 17 ወለል እንዲሁም ኮመርሻል የሚባለዉና የሁለገብ አገለግሎት ህንጻ ደግሞ ባለሁለት ወለል ነው፡፡

ከዋና ዋና አገልግሎት አስጣጥ አንጻር ህንጻዎቹ ከ 3000 በላይ ሰራትኞችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው ሲሆን አሁን ክ2500 በላይ ስራተኞችን እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ የ ተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎች፤ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ላብራቶሪዎች፤ ዘመናዊና ግዙፍ የዳታ ማእክል፤ በአለም አቀፍ እውቅና ሰጪዎች ተመዝኖ አክሬዲት የሚደረግ ቁልፍ የመንግስት መሰረት ልማት (PKI)፤ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል፤ ኤግዚብሽን ማዕከላት፤ ደረጃውን የጠበቀ የህፃናት ማቆያ፤ ክሊኒክ፤ የመሰብስቢያ አዳራሽ፤ ካፍቴሪያ፤ በተለያዩ ወለሎች ላይ ያሉ ሚኒ ካፌዎች፤ ስልጠናንስ ወርክሾፕ መስጫ ክፍሎችንም አካቶ ይዟል፡፡

በተጨማሪም ይህ ግንባታ ከተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ነጻ አንዲሆን ተደርጎ የተሰራና በተለይም ደግሞ ርዕደ-መሬትን መቋቋም እንዲችል ተደርጎ ዲዛይን ከተደረጉት በሃገሪቱ ዉስጥ ካሉት ጥቂት መሰል ግንባታዎች መካከል አንዱ ነው ለማለት ይቻላል፡፡

ክቡር ጠ/ሚ፤ ክቡራትና ክቡራን

በመጨረሻም ይህ የግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ዋጋ ለከፈላችሁ፣ በሃሳብ፣ በጉልበት፣ በገንዘብ ላገዛችሁን ወገኖችና ተቋማት፤ እንዲሁም ህንፃው ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በመግባትና ባልተመቸ ሁኔታም ዉስጥ እንኳን ሆናችሁ መደበኛ ስራችሁን ስታከናዉኑ ለነበራቸሁ ሰራተኞቻችን እና በአንድም በሌላም መንገድ አሻራችሁን በማኖር የህንፃው የታሪክ አካል ለሆናችሁ ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የራሱ ሕንጻ እንዲኖረው ክቡር ጠ/ሚ እርስዎ የግንባታውን ዲዛይን ሲያስተዋውቁ ከ ዛሬ 11 አመት በፊት እንዲህ ብለው መናገርዎትን መቅረጸ-ድምጽና ምስል ለታሪክ ከትቦ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ እርስዎ የተናገሩትን እንዳለ ቃል በቃል እንድጠቀም ይፈቀድልኝ፡፡ እንዲህ ብለው ነበር“....የሚያስከፍለንን ዋጋ ሁሉ ከፍለን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ህንጻ እንገነባለን....” ብለው ነበር፡፡

እነሆ እርስዎ እንደተናገሩት ህልምዎ ሰምሮ ለሚቀጠለዉም ትውልድ መሰረት ተጥሏልና እኔም በዚህ እርስዎ አርግዝዉት በነበረው ትውልድ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

በድጋሚ እንኳን ድስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን፤ አመሰግናለሁ፡፡

 

 

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ Thu, 6 May 2021
በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ
  • 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን እኩይ ሴራ ማክሸፉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ Thu, 6 May 2021
6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን እኩይ ሴራ ማክሸፉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ
  • ወቅታዊ ሁኔታዎችን በሚመለከት የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ Mon, 26 Apr 2021
ወቅታዊ ሁኔታዎችን በሚመለከት የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

Asset Publisher

Asset Publisher