የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ

Nested Applications

Asset Publisher

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና ከፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሙ

 

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬዉ እለት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የኮርፖሬሽኑን መሰረተ-ልማት ወደ ዲጂታል ስርአት እንዲገባ የማድረግ እና የሳይበር ልማት ስትራቴጂክ ሮድ-ማፕ(ፍኖተ-ካርታ) የማዘጋጀት እንዲሁም የመረጃዎቹን ደህንነት ማስጠበቅን ያካተተ እንደሆነ ታዉቋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በስምምነቱ ወቅት መሬት ዋነኛ ሀብት በመሆኑ የዚህን ሀብት መረጃ በተገቢው መንገድ መጠቀም እና ማስቀመጥ ለሀገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ሹመቴ አክለውም መረጃ አሁን ባለንበት ዘመን ትልቁ እና ቁልፍ መወዳደሪያ እንደሆነ ጠቁመዉ ይህንን መረጃ ደህንነቱን ለማስጠበቅ እና ለመጠቀም የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በሚያከናውናቸው ስራዎች ላይ ኤጀንሲው በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በበኩላቸዉ ትልቅ ሀብት የሆነው የመሬት ነክ መረጃ መያዝ ሀገራችን በምታከናውናቸው የመሰረተ- ልማት ስራዎች ላይ ጥራት ያለው ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለውም ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር የተደረገው ስምምነት የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በቴክኖሎጂ ራሱን ለማዘመን በሚከውናቸው ሰራዎች ላይ ማእከል ያደረገ ሲሆን በተለይ መረጃን ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ጠቅሰዋል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ Wed, 27 Jan 2021
የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ
  • የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ Wed, 30 Dec 2020
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
  • ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ Wed, 23 Dec 2020
ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ

Asset Publisher

Asset Publisher