የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ

Nested Applications

Asset Publisher

null የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፡ ጥር 19፣ 2013 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር በመተባበር ለፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የአንድ ቀን የገንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ባስተላለፉት መልዕክት የሳይበር ምህዳር በየጊዜው ተለዋዋጭ በመሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የሳይበር ጥቃት ወንጀል ነው ያሉት ዶ/ር ይናገር ደሴ በተለይም በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ጥቃት ከመፈፀሙ አስቀድሞ የመከላከል ሥራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አያይዘውም በፋይናንስ ዘርፍ የሚቃጣን ጥቃት ለመከላከል በባለድርሻ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እንደሚገባ እና ባንኮች ተገቢውን የአሠራር ሥርዓት ሊዘረጉ፣ በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል ሊያፈሩ እና ያላቸውን ቴክኖሎጂ በፍጥነት በመፈተሽ ብቃት ያለው መሠረተ-ልማት ሊገነቡ ይገባል ሲሉ ዶ/ር ይናገር ጠቁመዋል፡፡

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው የፋይናንስ ተቋማት ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ በቀዳሚነት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ በመሆናቸው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ይህ ስልጠናም የፋይናንስ ተቋማት ምን ዓይነት የሰው ኃይል፣ የአሠራር ሥርዓት እና ቴክኖሎጂ ሊኖራቸው እንደሚገባ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በቀጣይ ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመካላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ለዚህ እውን መሆን በተለይም የዘርፉ አመራሮች የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ የሥራቸው ቁልፍ ጉዳይ አድርገው በተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰሩም ለማስገንዘብ መሆኑንም ዶ/ር ሹመቴ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው በዋናነት ስለሳይበር ምንነት፣ ባህሪ እና በሌሎች ከሳይበር ደህንነት ዙሪያ ትኩረት በሚሹ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ Wed, 27 Jan 2021
የፋይናንስ ተቋማት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለጸ
  • የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ Wed, 30 Dec 2020
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
  • ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ Wed, 23 Dec 2020
ኤጀንሲው እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎች የመንግስት ተቋማት በአርዓያነት የሚገለፅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ገለፀ

Asset Publisher

Asset Publisher