አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ

Nested Applications

Asset Publisher

null አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ

 

አዲስ አበባ ህዳር 10/2013፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) አመራሮች እና ሰራተኞች በአለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በኤጀንሲዉ ደረጃ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ የጸረ-ሙስና ቀንን በተለያዩ ፕሮግራሞች አክብረዋል፡፡

የዘንድሮው የጸረ-ሙስና ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ "የትዉልድ የስነ-ምግባር ግንባታ በጠንካራ ዲስፕሊን በመምራት ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለን" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ሙስና ከአለም አቀፍ ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑን አንስተዉ ይህን ብልሹ አሰራር ከራስ በመጀመር እና ታማኝነት በማሳየት ጭምር ብቻ ሊቀንስ ብሎም ሊወገድ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በእለቱ በኤጀንሲዉ የበለጸገ ዲጂታል የጥቆማ መቀበያና ሃብት ማስመዝገቢያ ስርኣት ይፋ ተደርጓል፡፡ ይህ ስርአት የኢጀንሲዉ ሰራተኞች እና አመራሮች በያሉበት ቦታ ሆነዉ ጥቆማ የመስጠት፣ ሃብት የማስመዝገብ እና ሪፖርቶችን መከታተል ያስችላቸዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ስርአቱ ሰዎች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ከሙስና ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መጠቆም የሚያስችል በመሆኑ የኤጀንሲዉ አመራሮችም ሆኑ ሰራተኞች በነጻነት መረጃዎችን እንዲሰጡ እና በሚደረገዉ የጸረ ሙስና እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ማድረግ አንደሚያስችላቸው ዶ/ር ሹመቴ ገልጸዋል፡፡

በኤጀንሲው የጸረ ሙስና መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማኖ ገነሞ በበኩላቸው በተቋሙ የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ከፍተኛ አመራሩ እና የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እንዲሁም የተቋማችን አባላት በሙሉ ያላሰለሰ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፌደራል ስነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ኤጀንሲዉ በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ላለዉ ጸረ ሙስና እንቅስቃሴ የራሱን ሰራተኞች ሃብት ከማስመዝገብ አልፎ ለጸረ ሙስና ትግሉ አጋዥ የሆነ ዲጂታል ስርዓት በመተግበሩ አመስግነዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ አሁን ኤጀንሲዉ ተግባራዊ ያደረገዉን ዲጂታል የጥቆማ መቀበያና ሃብት ማስመዝገቢያ ስርኣት ወደ ሌሎች ፌደራል እና ክልል ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ ከኢመደኤ ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ም/ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የኤንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉን ጨምሮ ም/ዋና ዳይሬክተሮች እና በየደረጃ የሚገኙ የኤጀንሲው የሥራ ሃላፊዎች ሃብታቸዉን አስመዝግበዋል፡፡

Asset Publisher

Asset Publisher

News

  • በህወሀት ጁንታ ቡድን አማካይነት በቀን እስከ 25ሺህ የሀሰት መረጃዎች በቲውተር ሲሰራጭ እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ Fri, 18 Dec 2020
በህወሀት ጁንታ ቡድን አማካይነት በቀን እስከ 25ሺህ የሀሰት መረጃዎች በቲውተር ሲሰራጭ እንደነበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለጸ
  • ኤጀንሲው የህጻናት፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገጸ Wed, 2 Dec 2020
ኤጀንሲው የህጻናት፣ የወጣቶች እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገጸ
  • አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ Tue, 24 Nov 2020
አለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተከበረ

Asset Publisher

Asset Publisher