Asset Publisher

ኢመደኤ “የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) መከታተያና መቆጣጠሪያ ሲስትም” አዘጋጀ

 

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 13 ቀን 2012 : ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ሥርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጊዜ የማይሰጥ ርብርብ ለማገዝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) “የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮቪድ19 መቆጣጠሪያ ስርአት - Ethiopian COVID-19 Monitoring Platform” አዘጋጅቷል::

ኤጀንሲው ያዘጋጀው ሲስተም የተለያዩ መረጃዎችን የሚሰጥ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም፦

 • ሃገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ወቅታዊ covid-19 መረጃዎችን ለመከታተል፤
 • ገላጭ በሆኑ የቦታ ማሳያ መረጃዎች ለማየት፤
 • ስለ covid-19 ምልክቶች፣ ጥንቃቄዎች፣ ህክምናዎች እና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት፤
 • ዜጎች በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ላይ የሚያጋጥሟቸውን ጥርጣሬዎች ሪፖርት ለማድረግ፤
 • የተለያዩ ሙያ እና አቅም ያላቸውን በጎ ፈቃደኞች ለመመዝገብ፤
 • የተለያዩ እርዳታዎችን (በአይነትም ሆነ በገንዘብ) ለመሰብሰብ፤
 • ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ መረጃ ያላቸውን ምንጮችን (ሊንኮችን) ለመጠቆም፤
 • አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ-ልማቶችን (ሆስፒታል፣ ፋርማሲ፣ ፖሊስ ጣቢያ) ለማመላከት፤ እንዲሁም ሌሎችን መረጃዎች ለማሰራጨት የሚያገለግል ሲስተም ነው፡፡

የመከላከያና መቆጣሪያ ሲስተሙ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለውን የከፋ ሁኔታ ከወዲሁ ለመከላከልና ጥንቃቄ ለማድረግ በሚል የተዘጋጀ ሲሆን፤ በነገው ዕለት መጋቢት 14 ቀን 2012 / የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ይሆናል፡፡

በዚሁ አጋጣሚ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሃገራዊ ርብርብ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ-ኢመደኤ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ይገልጻል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
 • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
 • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
 • በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን? Wed, 25 Sep 2019