ጉግል በሦስት ወራት ውስጥ 12,000 የሳይበር ጥቃት ማስጠንቀቂያዎችን መላኩ ተሰማ - Disp
Asset Publisher
አዲስ አበባ፤ህዳር 18/2012፡ በሦስት ወራት ውስጥ በመንግስት የተደገፉ ከ10,000 በላይ የመረጃ ማጥመድ (phishing) ሙከራዎች እንደተፈፀሙ የገለጸው ጉግል በመላው ዓለም ለሚገኙ ተጠቃሚዎቹ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለመላክ መገደዱን አሳውቋል፡፡
የግዝፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ Threat Analysis Group (TAG)/ ዳይሬክተር የሆኑት ሻኔ ሀንትሌይ ካለፈው ሐምሌ እስከ መስከረም መጨረሻ 12,000 ማስጠንቀቂያዎችን በ149 ሀገራት ለሚገኙ ተጠቃሚዎች መላኩን ገልጸዋል፡፡
ከ90 በመቶ በላይ የሆኑት የመረጃ ወጥመድ (phishing) ጥቃቶች የተጠቃሚዎችን ሚስጥራዊ እና ግላዊ መረጃዎችን ለማጥመድ በማሰብ የሚላኩ ኢ-ሜሎች ናቸው፡፡ እነዚህ በኢ-ሜይል አማካኝነት የሚፈጸሙ ጥቃቶች ብዙ ጊዜ ትክክለኛ እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃልን ወይም ሌላ ለጥቃት የተጋለጠ ወሳኝ አካውንቶችን ለማግኘት የሚፈጸሙ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በተለየ መልኩ ለመረጃ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾች እና ፖለቲከኞች ከፍተኛ የደህንነት መቆጣጠሪያ ሥርዓት ሊኖራቸው እንደሚገባ ሻኔ ሀንትሌይ አሳስበዋል፡፡
የመረጃ አሰባሰብ ስርአትን የሚያስተጓጉሉ፣ የአይፒ አድርሻን የመመዝበር፣ ተቃዋሚዎችን እና አክቲቪስቶችን ያነጣጠሩ እንቅስቃሴዎች፣ አውዳሚ የሳይበር ጥቃቶችን እንዲሁም በተደራጀ መልኩ የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚያሰራጩ በ50 ሃገራት የሚንቀሳቀሱ እና 270 የሚሆኑ ተልዕኮ የተሰጣቸው እና በመንግስት የሚደገፉ የወንጀለኛ ቡድኖችን መለየቱን ታግ ኩባንያ ገልጿል፡፡
የተለያዩ የመረጃ ማሰራጫዎችን በመጠቀም ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ፍላጎት የሚያስጠብቁ መልዕክቶች እንዲሠራጩ መደረጋቸውን የተጠቆመ ሲሆን ከዚህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን 15 የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲወገዱ መደረጉን ሻኔ ሀንትሌይ ተናግረዋል፡፡
የጥቃት ሙከራዎቹ በዋናነት በአሜሪካ፣ በደቡብ ኮሪያ፣ በፓኪስታን እና በቪትናም ላይ እንደተፈፀሙ ተግልጿል፡፡ infosecurity-magazine
Most Viewed Assets
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
-
Thu, 26 Sep 2019ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
-
Wed, 25 Sep 2019ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
-
Wed, 25 Sep 2019በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?