Asset Publisher

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አባላት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ ስነ-ሥርዓቶች አከበሩ

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2012፡-በሀገራችን ለ44ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ109ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀንን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አባላት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች አክብረዋል፡፡


ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለበዓሉ ተሳታፊዎች የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


ሴቶች የሚያበረክቷቸው አስተዋፅዖች በወንዶች ሊተኩ አይችሉም ያሉት ዶ/ር ሹመቴ ዓለማችን ሴቶች በሚገባቸው ልክ እንዲሳተፉ ባለማድረጓ ልታድግ በሚገባት ልክ እንዳታድግ አድርጓታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የኢመደኤ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሴቶችን እኩል ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያየ መስክ እየሠራ ያለው ስራ መልካም በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡


በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ መምህርት ወ/ሮ አባይ አከማቸው የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ ዳራ፣ የሴቶች ቀን መከበር ያለው ፋይዳ እና የሴቶች እኩልነት እንዲረጋገጥ ከእያንዳንዱ አካል በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


ጋዜጠኛና ደራሲ እምወድሽ በቀለ የህይወት ተሞክሯቸውን እና አሁን የሴቶች መብት እንዲረጋገጥ በሚሠሯቸው ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ለኢመደኤ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡


በኢመደኤ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፅጌሬዳ ወርቁ በዳይሬክቶሬታቸው ስለተሠሩ የተለያዩ ሥራዎች ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /March 8/ “የሴቶች ደህንነትና መብት መከበር ለሰላማችንና ለህልውናችን መሠረት ነው!!” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ44ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ “እኔ የሴቶችን መብት የሚያከብር ትውልድ አካል ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ለ109ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

 

 

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
  • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
  • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
  • በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን? Wed, 25 Sep 2019