Asset Publisher

ጋሻ የተባለ 'ጸረ-ቫይረስ' በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መበልፀጉ ተነገረ

 

አዲስ አበባ ህዳር 10/2012፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በኔትወርክ እና በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ባሉ መተግበሪያዎች የሚመጡ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል “ጋሻ” የተባለ አንቲ-ቫይረስ ማበልፀጉ ተነገረ፡፡
የኢመደኤ የሳይበር ዴቨሎፕመንት ዳይሬክቶሬት የኢንፎርሜሽን ደህንነት ባለሙያ አቶ ናምሩድ ከሰተብርሃን ከኤጀንሲው የሳይበርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ጋሻ አንቲ ቫይረስ በኤጀንሲው መበልፀጉን ተናግረዋል፡፡
አንቲ-ቫይረሱ በሀገራችን ላይ የሚቃጡ የቫይረስ ዓይነቶችን ታሳቢ በማድረግ እና ዓለም ላይ አሉ የተባሉ ዋነኛ የቫይረስ ዓይነቶችን እንዲከላከል ተስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ባለሙያው ገልፀዋል፡፡
“ጋሻ” አንድን የቫይረስ ዓይነት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን መከላከል እንዲችል ታሳቢ ተደርጎ መሠራቱ ታውቋል፡፡
መተግበሪያው በሀገር ውስጥ መሠራቱ የራስ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ ለደህንነት ማስጠበቂያ ተብለው ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶች በራሳቸው የደህንነት ሥጋት የሚሆኑበትን አጋጣሚ የሚያስቀር ነው፡፡
መተግበሪያው አስፈላጊውን የብቃት ፍተሻ ሂደት ካጠናቀቀ በኋላ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍበት አግባብ እንደሚፈጠር አቶ ናምሩድ ተናግረዋል፡፡
ኢመደኤ በአዋጅ ከተሰጡት ሥልጣንና ኃላፊነቶች አንዱ የኢንፎርሜሽን መሠረተ ልማቶችን እና ሥርዓቶችን ማበልፀግና መዘርጋት ይገኝበታል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
  • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
  • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
  • በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን? Wed, 25 Sep 2019

Asset Publisher

ዜና

  • በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የተቃጣው የሳይበር ጥቃት ከ200 በላይ በሆኑ ጥቃት አድራሾች የተከሰተ ነው Fri, 6 Dec 2019
በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የተቃጣው የሳይበር ጥቃት ከ200 በላይ በሆኑ ጥቃት አድራሾች የተከሰተ ነው
  • በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፍ ተቻለ Thu, 5 Dec 2019
በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፍ ተቻለ
  • ጉግል በሦስት ወራት ውስጥ 12,000 የሳይበር ጥቃት ማስጠንቀቂያዎችን መላኩ ተሰማ Fri, 29 Nov 2019
ጉግል በሦስት ወራት ውስጥ 12,000 የሳይበር ጥቃት ማስጠንቀቂያዎችን መላኩ ተሰማ