Asset Publisher

የሰላም እና የደህንነት ተቋማት የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ፕሮግራም ሊቀርፁ እንደሚገባ ተገለፀ

 

 

የሰላምና ደህንነት ተቋማት የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ፕሮግራም ሊቀርፁ እንደሚገባ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በተካሄደ ወርክሾፕ ላይ ተገለፀ፡፡

የሰላምና ደህንነት ተቋማት የሳይበር ምህዳሩን ባህሪያት ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ሊገነዘቡ እንዲሁም ሳይበር ለሀገር ያለውን አወንታዊና አሉታዊ አስተዋፅኦ ለይተው ተገቢውን እርምጃ ሊወስዱ በሚያስችል ቁመና ላይ ሊገኙ ይገባል ተብሏል፡፡

በወርክሾፑ የሃገራችን የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ደረጃ ለመረዳት በኤጀንሲው 2011 . የተደረገን ጥናት እንደ መነሻ የተወሰደ ሲሆን በጥናቱ ከተካተቱ በፌደራል እና በክልል ተቋማት የተሰበሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛዎቹ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ግንዛቤያቸው ዝቅተኛ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በጥናቱ በተቋማት የታዩ ክፍተቶች መካከል ዝቅተኛ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና እና ትኩረት ፣የሳይበር ደህንነት አመራር እና አስተዳደር ስርዓት አለመኖር ፣የሳይበር ምህዳሩን ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ያለመኖር እንዲሁም ማእቀፎች አለመኖር ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

በሰላም እና ደህንነት ላይ የተሰማሩ አካላት ወቅቱ የሚጠይቀውን የሳይበር ደህንነት እውቀት ከመያዝ ባሻገር በሳይበር ምህዳሩ ሊፈጠሩ የሚችሉ ተጋላጭነቶችን እና አደጋዎችን መቀነስ የሚያስችል የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ማእቀፎችን በመቅረጽ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡

 

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
  • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
  • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
  • በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን? Wed, 25 Sep 2019

Asset Publisher

ዜና

  • “ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የነበረው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ሳምንት ስኬታማ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለፀ Tue, 12 Nov 2019
“ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የነበረው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ሳምንት ስኬታማ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለፀ
  • የሰላም እና የደህንነት ተቋማት የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ፕሮግራም ሊቀርፁ እንደሚገባ ተገለፀ Fri, 8 Nov 2019
የሰላም እና የደህንነት ተቋማት የተቀናጀ የሳይበር ደህንነት ፕሮግራም ሊቀርፁ እንደሚገባ ተገለፀ
  • ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሳይበር ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ተካሄደ Thu, 7 Nov 2019
ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሳይበር ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ተካሄደ