Asset Publisher

ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሳይበር ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ተካሄደ

 

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመከበር ላይ የሚገኘውን የብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ሳምንት ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ አካሄደ፡፡

በወርክሾፑ በኢመደኤ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተስፋዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለመገናኛ ብዙሃን የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ማካሄድ ያስፈለገበትን ዓላማ በመግለፅ መገናኛ ብዙሃን የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ የሳይበር ደህንነትን የስራቸው አንዱ የትኩረት አቅጣጫ አድርገው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢመደኤ የሳይበር ደህንነት ባለሙያ አቶ አብርሃም ተስፋዬ በሳይበር ደህንነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሑፍ ያቀረቡ ሲሆን በገለጻቸው ስለሳይበርና የሳይበር ደህንነት ምንነት፣ ዋና ዋና የሳይበር ተጋላጭነቶች፣ የሳይበር ጥቃቶችና ተፅዕኖዎች እንዲሁም አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ ተሞክሮዎችን በማቅረብ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

የሳይበር ጋዜጠኝነትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋክሊቲ የሳይበር ደህንነት አስተባባሪ አቶ ነብያት ፍቅሩ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በገለጻቸው የጋዜጠኝነት ሥራ ወደ ሳይበር ምህዳር እየተለወጠ በመምጣቱ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋማት በፖሊሲ ደረጃ አስገዳጅ ጠንካራ የይለፍ-ቃል ሊጠቀሙ፣ የሰለጠነ የደህንነት ባለሙያ ሊኖራቸው፣ የምስጠራ ቴክኖሎጂ (Encryption) ሊጠቀሙ እና ድረ-ገጾቻቸውን በየጊዜው ኦዲት ሊያስደርጉ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

በሌላ በኩል ጋዜጠኞች የሀገርን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር የህብረተሰቡን ንቃተ-ህሊና የማሳደግ ሚናቸውን ሊወጡ እና በሚደርሱ ጥቃቶች አዘጋገብ ዙሪያ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አቶ ነቢያት አሳስበዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

Cybergna season 01 Ep 01 P2
  • Cybergna season 01 Ep 01 P2 Tue, 1 Oct 2019
ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
  • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
  • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019