Asset Publisher

የሳይበር ደህንነት ለኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች
 • ደህንነት ከኮምፒዉተሮች ባለፈ ለመገልገያዎች ለምን አስፈለገ?

ይህን ጥየቄ ስናነሳ የሳይበር ደህንነት ከኮምፒዉተሮች ባለፈ ለመገልገያዎች ለምን አስፈለገ ብቻ ሳይሆን እያልን ያለነዉ ኮምፒዉተሮች ከተለመዱት የዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ አገልግሎት ፕላት ፎርሞች በዘለለ አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሆነ እየተመለከትን መሆኑን ነዉ፡፡ ብዙ መገልገያዎቻችን ኮምፒዉተር እየሆኑ ነዉ፤ ከሞባይል ስልኮቻችን እስከ ቪዲዮ ጌሞች እንዲሁም የመኪና ናቪጌሽን ሲስተሞችና ሌላም ሌላም መገልገያዎቻችን የኮምፒዉተር አገልግሎቶችን እየሰጡን ነዉ፡፡

ታዲያ ከእነዚህ የቴክኖሎጂ ጥቅሞች ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃት ትልቅ ስጋት እየሆነ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ከሳይበር ጥቃት ነፃ የምንላቸዉ መገልገያዎችም ጭምር ኢላማ ዉስጥ እየገቡ መጥተዋል፡፡

በተለይም የኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) ጥቅም ላይ ከማዋል ጋር ተያይዞ የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች እነዚህ መገልገያዎቻችንን በመጠቀም የጥቃት ሰለባ ሊያደርጉን የሚችሉ ናቸው፡፡

ይህም የሆነዉ መረጃዎችን ከኮምፒዉተሮች በተጨማሪ በእነዚህ መገልገያዎች እያኖርን በመሆኑ ነዉ፡፡

 • የኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ለሳየበር ጥቃት ተጋላጭ ናቸዉ?

ማንኛዉም አይነት ኮምፒዉተራይዝድ የሆነ ኮምፖነንት (ክፍል) ያላቸዉ መገልገያዎች የሳይበር ጥቃት ኢላማዎች ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን በተለይ ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት መፍጠር የሚያስችል መለያ ያለቸዉ መገልገያዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግባቸዉ ይገባል፡፡

በተጨማሪ ብዙ መረጃዎቻችን ሊኖሩበት የሚችሉ መገልገያዎችን በተለየ ሁኔታ ደህንነታቸዉን መጠበቅ ወሳኝ ነዉ፡፡

 • መገልገያዎችን ከጥቃት ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባናል?
 • መገልገያዎቹ አካላዊ ደህንነት መጠበቅ አለበት፡፡ የመገልገያዎቻችንን ደህንነት ከመጠበቅ በዘለለ ለሌላ ወገን እንዲደርስ መፍቀድ የለብንም፡፡
 • አፕሊኬሽኖች ሁሌም እኩል መዘመን አለባቸዉ ይህም አጥቂዎች ለማጥቀት እድል እንዳይፈጠርላቸዉ ለማድረግ ይረዳናል፡፡
 • የይለፍ ቃሎችና የመመስጠሪያ ዘዴዎችን መጠቀም ወሳኝ ነዉ፡፡ እንዲሁም የይለፍ ቃሎችን አስታዉስ የሚል ሴቲንግን አለመጠቀም መልካም ነዉ፤ ከተቻለ ድርብርብ አሊያም የባዮሜትሪክስ መለያ ዘዴዎችን መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡
 • መገናኛ መለያዎችን ማጥፋት፡፡ ለምሳሌ እንደ ብሉቱዝ ያሉ በርቀት ከሌሎች ኮምፒዉተሮች ጋር ለመገኛኘት የሚያስችሉ መለያዎችን ዝግ ማድረግ ተገቢ ሲሆን ይህም መገልገያዎችን ከሌሎች በምናገናኝበት ጊዜ ያለዉ ተጋላጭነት ከፍ ስለሚል ነዉ፡፡
 • ቢሆን መረጃዎችን መመስጠር (Encrypt) ማድረግ፤ ይህም መገልገያዎቻችን በአካል ብናጣቸዉ እንኳን መረጃዎቻችን ከተመሰጠሩ ከጉዳት ሊያተርፈን ስለሚችል ነዉ፡፡
 • ፐብሊክ ዋይፋይ ግንኙነቶችን በጥንቃቄ ማድረግም ወሳኝ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ግንኙነት ጊዜ ኔትዎርኩ ህጋዊና አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጥ፣ እጅግ በጣም ሚስጥራዊ ሊሆኑ የሚገባቸዉን የኦንላይን ተግባራት ከመፈፀም መቆጠብ ለምሳሌ የገንዘብ ነክ ጉዳዮችን እንዲሁም ደህንነታቸዉ የተጠበቁ ድረ-ገፆችን ብቻ መጠቀም ይመከራል፡፡

 

 

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ
 • ኢሞቴት ቫይረስ በድጋሚ መከሰቱ ተነገረ Thu, 26 Sep 2019
ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
 • ኢትዮጵያና እስራኤል በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል Wed, 25 Sep 2019
በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን?
 • በኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ላይ የተጋረጠውን የሳይበር ደህንነት ስጋት እንዴት መቅረፍ እንችላለን? Wed, 25 Sep 2019