doc

 • ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ መግለጫ

  ይህ ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ለሃገራችን ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ልማት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹ እና እምነት የሚጣልበት የሳይበር ወይም ኢንፎርሜሽን ከባቢ ለመፍጠር መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎችና እና ቁልፍ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በተመለከተ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የያዘ ሀገራዊ የደህንነት ማዕቀፍ/ሰነድ/  ነው፡፡ በተጨማሪ ሃገራችን በራሷ የሳይበር ክልል ውስጥ ያለ ኢንፎርሜሽን ምስጢራዊነት፣ ምልዑነት እና ተደራሽነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገባቸውን የደህንነት ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች በተመለከተ የሚወሰኑ ውሳኔዎች የያዘ ሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነድ ነው፡፡

  በመሆኑም ፖሊሲው ሰባት አንኳር የትኩረት አቅጣጫዎችን አካቷል፡፡ እነዚህም ህግና ቁጥጥር፣ ንቃተ ህሊና፣ የአቅም ግንባታ፣ ምርምርና ኢኖቬሽን፣ የዲጂታል ማንነትና የግላዊ መብት ጥበቃ፣ ቁልፍ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማቶች ጥበቃ እና ዓለም ዓቀፍና ሃገራዊ ትብብር ናቸው፡፡

  እነዚህን የትኩረት አቅጣጫዎች ግንዛቤ ውስጥ ያስገባና ዘመኑን የዋጀ ፖሊሲና ስትራቴጂ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ2004 ዓ.ም የወጣውን የኢንፎርሜሽን ደህንነት ፖሊሲ በማሻሻል ይህ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሊዘጋጅ ችሏል፡፡ 

    ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ

 • ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መምሪያ መግለጫ

  ይህ የማስፈጸሚያ መምሪያ ሃገሪቱ የሳይበር  ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ የተመላከቱ  ወቅታዊ እና መፃኢ ዕድሎችን ትክክለኛ አቅጣጫ እና ስትራቴጂ ተግባራዊነት፤ ፖሊሲ እና ስትራቴጂውን በአግባቡ ለመምራት፤ የመንግስት እና የግል አጋርነት ትብብር እንዲኖር ለማድረግ፤ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ፖሊሲውና ስትራቴጂውን ለማስፈጸም በሃገር ዓቀፍ ብሎም በአለም ዓቀፍ ደረጃ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ነው፡፡

  ስለሆነም ይህ የማስፈጸሚያ መምሪያ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ዓላማዎች፣ ግቦች፣ መርህዎችና አጠቃላይ ይዘት መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ለተግባራዊነቱ የዜጎችን፣ የመንግስትን፣ የግል ተቋማትን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት፣ የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ያስችላል፡፡

    ሃገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መምሪያ ለማውረድ እዚህ 

     ጋር ይጫኑ  

Asset Publisher

null የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ልዑክ በኢመደኤ የስራ ጉብኝት አደረገ

 

በደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር የተመራ የደቡብ ሱዳን የልዑካን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በመገኘት የስራ ጉብኝት እና ከተቋሙ የበላይ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡

ውይይቱ በዋናነት ሁለቱ ሃገራት በኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡

ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ስታገኝ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ እንደነበር ያወሱት የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር፤ አሁንም ቢሆን ደቡብ ሱዳን የተጠናከረ የሳይበር ደህንነት ተቋም እንዲኖራት በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዋል፡፡

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው የደቡብ ሱዳንን የኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነት በማጠናከር ረገድ በዋናነት በሦስት መሰረታዊ ጉዳዮች፤ ማለትም በሠው ሃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማት እና በአሰራር ሥርአት ዝርጋታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ሃገራዊም ይሁን ቀጠናዊ የኢንፎርሜሽንና ሳይበር ደህንነትን ለማርገጋጥ ሃገራት በጋራና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በውይይቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡