Asset Publisher

የሳይበር መረጃ

የሁላችንም ቤት ውስጥ አለ

የሁላችንም ቤት ውስጥ አለ

ዛሬ ዛሬ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከከተማ አልፈው ወደ ገጠሩ የአለም ክፍል የመዳረሳቸው አቅም እየሰፋ መጥቷል፡፡ በግለሰብ፣በቤተሰብ፣በማህበረሰብና በተቋማት ውስጥ በርካታ አይነት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተዳርሰዋል፡፡ የትምህርት፣የገንዘብ፣የፖለቲካ፣ማህበራዊ፣ስነ-ልቦናዊ ብሎም የሀገር ሉአላዊነት ጋር ከፍተኛ ጥምረት የፈጠረው የሳይበር ምህዳርም  በግለሰቦችም ደረጃ ሁሉን አቀፍ በመሆን ቤታችን ድረስ ገብቷል፡፡ በቴክኖሎጂ ውስጥ የገባ ማንኛውም ግለሰብ ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ነው፡፡

አንድ ግለሰብ የሚያደርጋቸው የገንዘብ ዝውውሮች፣አካውንቶች፣ማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ልውውጦች፣የሚጠቀማቸው የኮምፒውተር እና ዘመናዊ ስልኮች በሳይበር ወንጀለኞች የእይታ መረብ  ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነውም እያንዳንዱ ተጠቃሚ በሚያደርጋቸው ግላዊ የመረጃ ልውውጥ ሂደት ውስጥ በሚፈጥራቸው ክፍተቶች ምክንያት ነው፡፡ የሰው ልጅ በባህሪው ስልቹ፣የሚደክም፣የሚያምንና ነገሮችን ለማዎቅ ካለው ከፍተኛ ጉጉት አንፃር በርካታ ሙከራዎችን እና ስህተቶችን ይፈጥራል፡፡ እኒህም ክፍተቶች ለሳይበር ወንጀለኞች አዎንታዊ አጋጣሚዎች ናቸው፡፡  በመሆኑም ማንኛውም ሰው ቴክኖሎጂ እስከተጠቀመና በኢንተርኔት መረብ ውስጥ እስከተሳተፈ ድረስ የትምህርት፣ሚስጥራዊና ግላዊ የማንነት መረጃዎች እና ገንዘብ  በስጋት ውስጥ እንዳሉ በማሰብ ዘወትር በንቃት ሊጠቀም ይገባዋል፡፡ ከእነዚህም ጉዳዮች በለፈ የአንድ ሰው ስነ-ልቦናዊ ጤንነት በሳይበር ምህዳር ውስጥ ከአጠቃቀም ስህትት በሚመነጭ ሱሰኝነት አሊያም በሌሎች አካላት በሚደርስ የኦላይን ትንኮሳ ሊጎዳ ይችላል፡፡ በስነ-ልቦና የተጎዳ ሰው ደግሞ ከግላዊ እስከ ተቋማዊ ባሉ የህይዎት መስተጋብር ውስጥ የሚያልፉ ጠቃሚ መረጃዎችን ለመነጠቅ ቅርብ ነው፡፡ በአጠቃላ የሳይበር ምህዳር ከግለሰብ እስከ ሀገር ድረስ ትኩረትን የሚሻ ጉዳይ በሆኑ የመረጃ ደህንነትን ለማስጠበቅ የግለሰቦች የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ከፍ ማለት አስፈላጊ በመሆኑ፡፡ እርስዎ ሁሌም የሳይበር ምህዳር እድገትንና ደህንነትን ጠንቅቆ በማዎቅ የሚደርስብዎትን ችግር ቀድሞ የሚያዩ፣የሚረዱ ብሎም የመፍትሄ አካል የሚሆኑበትን አቅም ማጎልበት አስፈላጊ ነው፡፡