የሳይበር መረጃዎች

የሃገራችን ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ሃቆች

የኢመደኤ የሳይበር ደህንነት የንቃተ ህሊና ግንባታ ቡድን 2011 . በሰራው ሀገር-አቀፍ የሳይበር ደህንነት ምዘና ጥናት 1635 ሰውችን ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በማሳተፍና ሌሎችንም የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች በመጠቀም የተገኘው ውጤት እነዚህን ከሳይበር ደህንነትና የጥቃት ተጋላጪነት ጋር ክፍተኛ ቁርኝት ያቸውን ነጥቦች ያሳያል ፡፡

 • 975 (59.5 %) ያክሉ የጥናት ተሳታፊዎች ስልክ ቁጥርን እንደ ፓስወርድ መጠቀም ጠንካራ ፓስወርድ እንደመጠቀም እንደሚቆጥሩት ያሳያል ፡፡
 • /የህዝብ ዋይፋይ አገልግሎትን መጠቀም ችግር እንደሌለው 35 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊወች እንደሚያምኑ ያሳያል፡፡
 • 67.6 በመቶ የሚሆነው የጥናቱ ተሳታፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛ እንደሆኑ ያምናሉ ፡፡
 • 36.9 በመቶ መተግበሪያዎችን ትክክለኛታቸው ካልተረጋገጠ ምንጪ አውርዶ መጠቀም ለጥቃት የማያጋልጥ ተግባር እንደሆ ያምናሉ፡፡
 • 25.1 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች በይነ መረብ ላይ ክሊክ የምናደርጋቸውና የምንከፍታቸው ሊንኮች ለሳይበር ጥቃት ተጋላጪ እንደሚያደረጓቸው የማያውቁና የማያምኑ ናቸው ፡፡
 • 56.8 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች የመረጃ/የሳይበር ደህንነት የኢትዮጵያ ሃገራችን ስጋት እንደሆነ ያምናሉ ፡፡
 • 54.2 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ተመሳሳይ ፓስዎርድ ለብዙ አካዎንቶች መጠቀም ችግር እንደሌለው 14.8 የሚሆኑት ደግሞ ምንም እውቀት እንደሌላቸውና ቀሪዎቹ 31 በመቶ ያህሉ ደግሞ ትክክል እንዳልሆነ እንደሚያምኑ የጥናቱ ውጤት አሳይቷል ፡፡
 • 64.7 በመቶ ያህሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች ፓስዎርድን ከጓደኞች / ቤተሰብ /ስራ ባልደረቦቸ ባጋራ/ ባሳውቅ ችግር ይፈጥርብኛል ብየ አላምንም የሚሉ ሲሆን 12 በመቶዎቹ ደግሞ ምንም እንደማያውቁ ይናገራሉ ፡፡
 • 27.7 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች የሳይበር ጥቃት ፈጸሚዎች /ሃከሮች ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያምናሉ 16.3 በመቶ ያክሉ ምንም አያውቁም ቀሪዎቹ 55.8 በመቶ ያክሉ ግን እነሱ የአጥቂዎች ኢላማ ሊሆኑ እንደማይችሉ ያምናሉ፡፡
 • 59.1 በመቶ ያክሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች ፓስዎርዶቻቸውን የሚታይ ቦታ ላይ ጽፈው ማስቀመጥን እንደ ማስታወሻ መንገድ እንደሚጠቀሙበት አሳውቀዋል ፡፡
 • 50.2 በመቶ ያክሉ የዚህ ጥናት ተሳታፊዎች የኢሜል አታችመንቶችን ያለጥንቃቄ እንደሚከፍቱ ውጤቱ ያሳያል ፡፡

 • የሳይበር ደህንነት አስተሳሰቦች

ምንም እንኳን በዘመናችን ተቋማትና ግለሰቦች ለሳይበር ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ ቢሆንም በሳይበሩ ምህዳር ተጠቃሚ ግለሰቦችና በተቋማት ላይ በሚስተዋሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሳይበር ጥቃቶች እየተከሰቱ እንደሆነ እንዲከሰቱም ምክንያት የመሆን እድላቸው ሰፊ እንደሆነ የሳይበር ሰኪውሪቲ ኤክስፐርቶች ያሳውቃሉ ከእንደዚህ አይነት የተሳሳቱ አስተሳሰቦች መካከል የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው -

 1. አነስተኛ ስለሆነ የሳይበር ጥቃት ሊደርስበት አይችልም የሚል ሃሳብ 
 2. ቫይረስና ጸረ ማልዌር ስለምጠቀም/ስለምንጠቀም ጥቃት ሊደርስብን አይችልም የምንጠቀማቸው መከላከያዎች በራሳቸው በቂ ናቸው የሚል ሀሳብ
 3. /የይለፍ ቃላችን በጣም ጠንካራ ስለሆነ ማንም ሊሰብረው ስለማይችል ለጥቃት አንጋለጥም
 4. ምንም አይነት የሳይበር ስጋት የለበትም የሚል ሃሳብ
 5. መጠቀሚያ ዲቫይሶችን ለድርጂት ስራ መጠቀም ችግር የለውም ወይም ለጥቃት ከመጋለጥ ሊከላከለን ይችላል ብሎ ማሰብ
 6. / የምጠቀምበት የሳይበር ደህንነት ሲስተም ፍጽም ነው የትኛውንም አይነት ጥቃት ይከላከላል ብሎ ማሰብ
 7. ሊመጣ የሚችለው ከተቋም ውጭ ብቻ ነው ብሎ ማሰብ
 8. ደህንነት ስራ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ክፍል ስራ ስለሆነ እነሱ ይሰሩታል /ይከታተሉታል ብሎ በማሰብ ጥንቃቄ አለማድረግ
 9. ደህንነት ስልጠናና ፍተሻ ለድርጂታችን/ ለምንጠቀምበት ሲስተም አያስፈልገንም/አያስፈልገኝም ብሎ ማሰብ
 10.   ሊጋልጡን የሚችሉ ነገሮችን በቀላሉ መለየት እንችላለን ብሎ ማሰብ  ናቸው ፡፡

 

Asset Publisher

የሳይበር መረጃ