የሳይበር ደህንነት ወር

የሳይበር ደህንነት  ሳምንት /ፕሮግራም/  አላማ

የሳይበር ደህንነት ሳምንት ዋና አላማ ቁልፍ ተቋማትንና ሰፊውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማሳደግ ሃገራዊ የሳይበር መከላከል አቅምን በመገንባት  ብሄራዊ የሳይበር ደህንት ሃይልን ለማጠናከር ነዉ፡፡ 

ይህን የሳይበር ደህንነት የንቃተ ህሊና ሳምንት ማክበር ያስፈለገበት ምክንያት የዜጎችን፣ የግልና የመንግሰት ቁልፍ ተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊናን በማሳደግ ብሄራዊ የሳይበር ደህንነት አቅምን ማጎልበት ስለሚያስችልና ይህን አለማቀፍ ዘመቻ ወደ ሌሎች ተቋማት ለማዛመት ስለሚያስችል ነው ።

የሳይበር ደህንነት የአለማችን አበይት ጉዳዮች ውስጥ ከገባ ብዙ ዓመታትን እያስቆጠረ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ መዘመን የሰውን ልጅ ሁለ-ገብ የሳይበር ስነ-ምህዳር  መስተጋብርን ከምንም ጊዜው በላይ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ ይህም እድገት የሳይበር ደህንነት ስጋትና ጥቃት መከሰትንም በአሉታዊ ገፅታው ይዞ መጥቷል፡፡ የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ከቁልፍ መሰረተ-ልማቶች በማለፍ በግለሰቦች ዘንድም አስፈላጊቱ የጎላ ነው፡፡ በመሆኑም በአለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ደህንነትን ወር ለ16ኛ ጊዜ የሳይበር ንቃተ-ህሊናን ከፍ ለማድረግ በማሰብ ይከበራል፡፡ በሀገራችንም ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥቅምት 24-30/2012ዓ.ም ትኩረት ለሳይበር ደህንነት በተሰኘ መፈክር የሚዘልቅ ንቅናቄ ይከበራል፡፡ አላማውም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እና ቁልፍ ተቋማት ለሳይበር ደህንነት ትኩረት በመስጠት ከግለሰብ እስከ ሀገር የሚደርሱ የሳይበር ደህንነት ጥቃትንና ስጋቶችን በማወቅ፣ በመከላከል እንዲሁም ምላሽ በመስጠት ራስን ከምህዳሩ ጋር አብሮ በማሳደግ የበኩሉን መወጣት እንዲችል ማድረግ ነው፡፡

 

የበዓሉ /ፕሮግራሙባለድርሻዎችና የሚጠበቁ ውጤቶች

በዚህ ፕሮገራም ላይ ኢመደኤ የሃገሪቱን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ ሃላፊነቱን ለመወጣት ዋና ባለድርሻ ሆኖ የሚደረጉ የንቃተ ህሊና መስጫ መርሃ ግብሮችን የሚከውን ሲሆን በቀጣይ ፕሮግራሙን ማስፋት እንዲቻል የሀገራችን ቁልፍ የግልና የመንግስት ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሳተፉ ይደረጋል ፡፡ በቀጣይ አመታትም እነዚህ ቁልፍ ተቋማት ሳምንቱን በራሳቸው የሰራተኞቻቸውንና የተገልጋዮቻቸውን የሳይበር ንቃተ ህሊና ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ እንዲያከብሩና ስራዎችን በዘላቂነት እንዲሰሩ የሚያስችል ማነቃቂያ ነዉ ፡፡

Asset Publisher

የሳይበር መረጃ