About Us

የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ክፍል

ሳይበር የቴክኖሎጂ፣የሰው ልጅና ሂደት ጥምር ውጤት ነው፡፡ በእነዚህ ሂደቶች ውስጥ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ ፈጣሪም፣ተጠቃሚምና ተጠቂም ነው፡፡ በሳይበር ምህዳር ውስጥ ከሚፈጠሩ ጥቃቶች 90 በመቶ የሚሆኑት በሰዎች ክፍተት አማካይነት የሚፈጠሩ በመሆናቸው፤የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊናን ማሳድግ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ቀዳሚውና ወሳኙ ተግባር ነው ፡፡በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ቡድን የሳይበር ጥቃትን መከላከል የሚችል የነቃ ማህበረሰብ ብሎም ባለሙያ ለመፍጠር የሚሰራ አካል ነው፡፡